ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

ከደቂቃዎች በኃላ የሚጀምረው የሸገር ደርቢ አሰላለፍ እና ተጨማሪ መረጃዎችን እነሆ።

ባሳለፍነው ሳምንት አራፊ የነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራተኛው ሳምንት ሰበታን ከረታበት ጨዋታ ግብ አስቆጥሮ የነበረው ጋዲሳ መብራቴን በአዲስ ግደይ ተክቶ ጨዋታውን ይጀምራል። አዲስ ለመጀመሪያ ጊዜ በተጠባባቂ ወንበር ላይ ጨዋታውን ይጀምራል።

አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ በሰበታው ጨዋታ ድል ያደረገውን ቡድን ሳይቀይር ጨዋታውን ይጀምራል ወጣቶቹ ሬድዋን ናስር እና ዊልያም ሰለሞንም በድጋሚ በመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ የመካተት ዕድልን አግኝተዋል።

የቡድኖቹ አሰላለፍ

ቅዱስ ጊዮርጊስ

30 ፓትሪክ ማታሲ
14 ሄኖክ አዱኛ
15 አስቻለው ታመነ
23 ምንተስኖት አዳነ
24 ኤድዊን ፍሪምፖንግ
5 ሐይደር ሸረፋ
20 ሙሉዓለም መስፍን
27 ሮቢን ንጋላንዴ
11 ጋዲሳ መብራቴ
10 አቤል ያለው
9 ጌታነህ ከበደ

ኢትዮጵያ ቡና

1 ተክለማርያም ሻንቆ
18 ኃይሌ ገብረትንሳይ
4 ወንድሜነህ ደረጄ
2 አበበ ጥላሁን
11 አሥራት ቱንጆ
16 ሬድዋን ናስር
13 ዊልያም ሰለሞን
5 ታፈሰ ሰለሞን
10 አበበከር ናስር
25 ሀብታሙ ታደሰ
17 አቤል ከበደ


© ሶከር ኢትዮጵያ