ከአምስተኛው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ በኋላ የቡድኖቹ አሰልጣኞች ለሶከር ኢትዮጵያ ይህንን ብለዋል።
አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ – ሀዲያ ሆሳዕና
ስለጨዋታው
በእንቅስቃሴ ደረጃ የሚማርክ አይደለም። የኃይል ጨዋታ የበዛበት ነው። ማሸነፉ ግን መልካም ነው።
በርካታ ተጫዋቾች ካመጡበት ከአዳማ ጋር ስለመግጠማቸው
ከቤተሰብ ጋር እንደመጫወት ነው። አዳማ ለእኔ ሁሉ ነገሬ ነው። ከህዝብ ጋርም ከአመራር ጋርም የነበረኝ ግንኙነት መልካም ነው። አዳማ ሁሌም መልካም ነገር እንዲገጥመው እመኛለሁ። በተከታታይ ዓመታት ለሜዳሊያ ያበቃሁት ቡድን ነው። ባለው የፋይናንስ ችግር ምክንያት ነው ሁላችንም ለመውጣት የተገደድነው እንጂ ጠልተነው አይደለም።
ስለዱላ መላቱ ጨዋታ ቀያሪነት
ዱላ ሙላቱን ያለምክንያት አይደለም የምጠቀምበት። በወሳኝ ጨዋታዎች ውጤታማ የሚያረገኝ ነው። ያ የእኔ የአሰራር ስልት ነው። ልጁን የምጠቀምበት የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አለ። እንደ አስፈላጊነቱ ከመጀመሪያም ልጠቀም የምችልባቸው ሁኔታዎች አሉ።
አሰልጣኝ አስቻለው ኃይለሚካኤል – አዳማ ከተማ
ስለጨዋታው
ጨዋታው ጥሩ ነበር። ኳሱን ተቆጣጥረን ለመጫወት ሞክረናል። ውጤት ለመቀየር አሸንፎ ለመውጣት ነበር የገባነው ከዕረፍት በኋላ ኳስ ነው እና አልተሳካም። በሚቀጥለው አሻሽለን ለመምጣት እንሞክራለን።
ስለግብ ጠባቂዎች መቀያየር
ያው ጉዳት ነው። በየጨዋታው ብዙ ጉዳት እየገጠመን ነው። ከነጉዳታቸው ነው እያጫወትናቸው ያላነው። ፍሰሀም አብዲሳም ጉዳት ላይ ሆነው ነው ያስገባናቸው። ሱለይማን አህመድም ጉዳት ላይ ነው። ሲሻላቸው ጥሩ ነገር ይዘን ለመምጣት እንሞክራለን።
© ሶከር ኢትዮጵያ