ስድስተኛ ሳምንት ላይ በደረሰው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ሒደት ሰበታ ከተማ በተለያዩ ጉዳዮች ቅሬታ አለኝ ሲል ደብዳቤ አስገብቷል።
ክለቡ ለሚዲያ አካላት በላከው የቅሬታ ደብዳቤ ውስጥ በዋናነት በዳኝነት በኩል በተለይ “ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረግነው ጨዋታ የፍፁም ገብረ ማርያም ጎል ከጨዋታ ውጭ ነው ብሎ የተሻረበት እና ኢትዮጵያ ቡና ያስቆጠረው ሦስተኛ ጎል ከጨዋታው ውጭ ሆኖ የታለፈበት መንገድ እና ሌሎች የዳኝነት ክፍቶችን ተመልክተናል። እንዲሁም የኮቪድ ፕሮቶኮልን ከ10 ደጋፊዎች እና የክለብ አመራሮች ያልበለጠ እንዲገባ የተፈቀደ ቢሆንም ከኢትዮጵያ ቡና በኩል ከ300 በላይ ደጋፊዎች እና አመራሮች የታደሙበት እንደነበረ ማስረጃዎች አሉን። በተጨማሪም በአዲስ አበባ ጎዳናዎች የተሰቀሉ Dstv ማስታወቂያዎች ባአብዛኛው ጥቂት ክለቦችን ብቻ ለማስተዋወቅ ሆን ተብሎ የተሰራ መሆኑን ተመልክተናል።” ይላል።
በደብዳቤው ላይ በቀረው የቅሬታ ፁሑፍ በማጠቃለያውም ውድድሩ ከወገንተኝነት ያልፀዳ መሆኑን ገልፆ እነዚህ ችግሮች አወዳዳሪው አካል እና ፌዴሬሽኑ በጥልቀት ተመልክቶ አስፈላጊውን የእርምት ማስተካከያ እንዲያደርግ በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።
የደብዳቤው ሙሉ ሀሳብ እንደሚከተለው ነው።
© ሶከር ኢትዮጵያ