አቤል ያለው ስለ ጉዳት ሁኔታው ይናገራል

ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት የሸገር ደርቢ ጨዋታ ላይ ጉዳት አስተናግዶ ተቀይሮ የወጣው ፈጣኑ አጥቂ አቤል ያለው ስለ ጉዳቱ ይናገራል።

በስድስተኛ ሳምንት የሊጉ ተጠባቂው የሸገር ደርቢ ጨዋታ ወቅት በመጠናቀቂያ አስራ አምስት ደቂቃ ሲቀረው ፈጣኑ አጥቂ አቤል ያለው ጉዳት አስተናግዶ በአማኑኤል ገብረሚካኤል ተቀይሮ መውጣቱ ይታወሳል። በዘንድሮ ዓመት የፈረሰኞቹ ወሳኝ ተጫዋች መሆኑን እያስመሰከረ የሚገኘው አቤል የጉዳቱ ዓይነት ምንድነው? ለቀጣይ ጨዋታ የመድረሱ ጉዳይስ እንዴት ነው? ብለን አጭር ጥያቄ አቅርበንለት ” ትንሽ ጡንቻዬ ላይ ግጭት ደርሶብኝ ነው ተቀይሬ የወጣሁት። አሁን በጣም ደህና ነኝ በቀጣይ ጨዋታዎች ላይ በሚገባ እደርሳለሁ።” ብሏል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ እስከ ስድስተኛው ሳምንት ድረስ ባስቆጠራቸው አስራ ሦስት ጎሎች ውስጥ አቤል ያለው ለጎል የሚሆኑ ኳሶች በማመቻቸት እና ጎል በማስቆጠር የነበረው ሚና የጎላ እንደሆነ ይታወቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ