የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሁለት ቀናት በኋላ ዝግጅቱን ይጀምራል

ዋልያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ አምስተኛ የምድብ ጨዋታ ቅድመ ዝግጅት ከወዲሁ ይጀምራሉ፡፡

በ2021 አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ አራት ጨዋታዎችን አድርጎ ስድስት ነጥቦች የሰበሰበው ብሔራዊ ቡድኑ ለቀጣዩ አምስተኛ የምድቡ ማጣሪያ መጋቢት ወር አጋማሽ ላይ ማዳጋስካርን በሜዳው የሚገጥም ሲሆን ለዚህም ጨዋታ ቅድመ ዝግጅት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለተጫዋቾች ጥሪ እንዳደረጉ ሰምተናል፡፡ ከሁለት ቀናት በኋላም ጥር 2 በጅማ ከተማ ዝግጅቱን እንደሚጀምር ታውቋል፡፡ አሰልጣኙ በኒጀሩ የማጣሪያ ጨዋታ ከጠሯቸው ተጫዋቾች በተጨማሪ አዳዲስ ዘጠኝ ተጫዋቾች በስብስቡ ማካተታቸውን ሰምተናል፡፡

በጥር ወር የሚደረገው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጅማ ላይ የሚከወን በመሆኑ ተጫዋቾቹ ባሉበት ጅማ ዝግጅት ለማድረግ እንደተመረጠ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል። በጥር ወር መጨረሻ እና የካቲት መጀመርያ ባሉ የሊግ ጨዋታ በማይደረግባቸው ክፍት ቀናት ተጨማሪ ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚችልም ፍንጭ የሚሰጥ ነው፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ