ሀዋሳ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

በቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ውሎ ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀምረው የሀዋሳ እና ድቻ አስላለፍ ይህን ይመስላል።

አሳልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ቡድናቸው ከጅማ አባ ጅፋር አቻ ከተለያየበት ጨዋታ የአራት ተጫዋቾች ለውጥ አድርገውል። በለውጡ ዳንኤል ደርቤን በተከላካይ መስመር በዘነበ ከድር ቦታ ሲተኩ አማካይ ክፍል ላይ ዳዊት ታደሰን በጋብርኤል አህመድ ቦታ በመጠቀም ያልተጠበቀ ለውጥ አድርገዋል። ከዚህ ውጪ ላለፉት ሳምንታት ጉዳት ላይ የሰነበተው መስፍን ታፈሰ የዮሀንስ ሴጌቦን ቦታ ተረክቧል። በኤፍሬም አሻሞ ምትክ ደግሞ ላውረንስ ላርቴ ተተክቷል።

አሰልጣኝ ደለለኝ ደቻሳ በበኩላቸው ከድሬዳዋ ከተማው ጨዋታ ባደረጉት ለውጥ ጉዳት አስተናግዶ ከሜዳ የወጣው ስንታየሁ መንግሥቱን ቤታ ለፀጋዬ ብርሀኑ በመስጠት ኤልያስ አህመድን ከህመም መልስ አስጀምረውታል። በተጨማሪም ያሬድ ዳርዛ እና አንተነህ ጉግሳ በእዮብ በቀታ እና እንድሪስ ሰዒድ ቦታ ሲተኩ ግብ ጠባቂው መክብብ ደገፉ እንዲሁም ተከላካዮቹ ደጉ ደበበ እና መሳይ አገኘው አርፈው ሰዒድ ሀብታሙ ፣ መልካሙ ቦጋለ እና ያሬድ ዳዊት ወደ ቀዳሚው አሰላለፍ መጥተዋል።

ሁለቱ ቡድኖች ይዘውት የሚገቡት አሰላለፍ ይህንን ይመስላል:-

ሀዋሳ ከተማ

1 ሜንሳህ ሶሆሆ
7 ዳንኤል ደርቤ
16 ወንድምአገኝ ማዕረግ
4 ምኞት ደበበ
26 ላውረንስ ላርቴ
12 ደስታ ዮሐንስ
3 ኤፍሬም ዘካርያስ
29 ወንድማገኝ ኃይሉ
18 ዳዊት ታደሰ
17 ብሩክ በየነ
10 መስፍን ታፈሰ

ወላይታ ድቻ

30 ሰዒድ ሀብታሙ

9 ያሬድ ዳዊት
15 መልካሙ ቦጋለ
16 አናጋው ባደግ
26 አንተነህ ጉግሳ
20 በረከት ወልዴ
28 አማኑኤል ተሾመ
6 ኤልያስ አህመድ
11 ያሬድ ዳርዛ
21 ቸርነት ጉግሳ
4 ፀጋዬ ብርሀኑ


© ሶከር ኢትዮጵያ