ፋሲል ከነማ ከ ሲዳማ ቡና – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

የስድስተኛ ሳምንት የረፋድ ጨዋታ ላይ ፋሲል እና ሲዳማ ወደ ሜዳ ይዘዋቸው የሚገቡ ተጫዋቾች ታውቀዋል።

በፋሲል ከነማ በኩል አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ ከባህር ዳር ጋር አቻ ከተለያየው ስብስባቸው ሰዒድ ሀሰን እና ሀብታሙ ተከስተን ወደ መጀመርያ አሰላለፍ ሲመልሱ እንየው ካሣሁን እና በረከት ደስታ ከአሰላለፉ ውጪ ሆነዋል።

በሲዳማ ቡና በኩል ናይጄርያዊው ተከላካይ ላውረንስ ኤድዋርድ የዓመቱ የመጀመርያ ጨዋታውን የሚያደርግ ሲሆን አማኑኤል እንዳለ፣ ያስር ሙገርዋ እና እሱባለው ሙሉጌታ በመጀመርያ አሰላለፍ የተካተቱ ተጫዋቾች ናቸው። ተመስገን በጅሮንድ፣ ዮሴፍ ዮሐንስ፣ አዲሱ አቱላ እና ጊት ጋትኮች ደግሞ ከአሰላለፉ ውጪ ሆነዋል።

አሰላለፍ

ፋሲል ከነማ

1 ሚኬል ሳማኬ
13 ሰዒድ ሀሰን
5 ከድር ኩሊባሊ
16 ያሬድ ባየህ
21 አምሳሉ ጥላሁን
14 ሀብታሙ ተከስተ
8 ይሁን እንደሻው
10 ሱራፌል ዳኛቸው
12 ሳሙኤል ዮሐንስ
19 ሽመክት ጉግሳ
26 ሙጂብ ቃሲም

ሲዳማ ቡና

30 መሳይ አያኖ
17 ዮናታን ፍሰሀ
34 ላውረንስ ኤድዋርድ
2 ፈቱዲን ጀማል
12 ግሩም አሰፋ
16 ብርሀኑ አሻሞ
10 ዳዊት ተፈራ
29 ያስር ሙገርዋ
3 አማኑኤል እንዳለ
20 እሱባለው ሙሉጌታ
9 ሀብታሙ ገዛኸኝ


© ሶከር ኢትዮጵያ