ወልቂጤ ከተማ ከ ሀዲያ ሆሳዕና – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

የስድስተኛው ሳምንት የመጨረሻ መርሐ-ግብር የሆነው የወልቂጤ እና ሀዲያ ሆሳዕና አሰላለፍ ታውቋል።

አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ቡድናቸው ደካማ አቋም አሳይቶ በተሸነፈበት የሲዳማው ጨዋታ ከተጠቀሙበት አሰላለፍ የሦስት ተጫዋቾች ለውጥ አድርገዋል። በዚህም ጉዳት የገጠማቸው ስዩም ተስፋዬ እና አሚን ነስሩን በተስፋዬ ነጋሽ እና ዳግም ንጉሤ ሲተኩ ፊት መስመር ላይ የአብዱርሀማን ሙባረክን ቦታ ለሄኖክ አየለ ሰጥተዋል።

በ100% ድል ላይ የሚገኙት ሀዲያ ሆሳዕናዎች ከተጠባባቂ ወንበር እየተነሳ በጎ ተፅዕኖውን በማሳየት ላይ የሚገኘው ዱላ ሙላቱን በካሉሻ አልሀሰን ምትክ አስጀምረዋል። አዳማ ከተማን ከረቱበት ጨዋታ ባደረጉት ሌላኛው ለውጥ መድሀኔ ብርሀኔን በመተካት ሄኖክ አርፌጬ የመስመር ተከላካይነት ቦታውን ይዟል።

ቡድኖቹ ወደ ሜዳ ይዘውት የሚገቡት አሰላለፍ ይሄን ይመስላል።

ወልቂጤ ከተማ

1 ጀማል ጣሰው
12 ተስፋዬ ነጋሽ
30 ቶማስ ስምረቱ
19 ዳግም ንጉሤ
3 ረመዳን የሱፍ
21 ሀብታሙ ሸዋለም
18 በኃይሉ ተሻገር
14 አብዱልከሪም ወርቁ
13 ፍሬው ሰለሞን
20 ያሬድ ታደሰ
26 ሄኖክ አየለ

ሀዲያ ሆሳዕና

32 ደረጄ ዓለሙ
2 ሱሌይማን ሀሚድ
5 አይዛክ ኢሴንዴ
25 ተስፋዬ በቀለ
17 ሄኖክ አርፊጮ
21 ተስፋዬ አለባቸው
10 አማኑኤል ጎበና
7 ዱላ ሙላቱ
22 ቢስማርክ አፒያ
20 ሳሊፉ ፎፋና
12 ዳዋ ሆቴሳ


© ሶከር ኢትዮጵያ