ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | አቃቂ ቃሊቲ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረመ

በአሰልጣኝ ብዙዓየው ዋዳ የሚመራው አቃቂ ቃሊቲ ሁለት ተጫዋቾችን በእጁ አስገብቷል፡፡

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን በሀዋሳ እየተደረገ ይገኛል በውድድሩ ላይ የሁለተኛ አመት ተሳትፎን ከሁለተኛ ዲቪዚዮን ካደገ በኃላ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ዘንድሮ በሊጉ በእንቅስቃሴ መልካም የሚባል የውድድር ጊዜን እያሳለፈ ቢሆንም ጎል በማስቆጠሩ ረገድ ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ድክመት ታይቶበታል። ለዚህም ክለቡ ካለበት የውጤት ቀውስ ለመውጣት ይረዳው ዘንድ ሁለት ተጫዋቾችን ከመቐለ 70 እንደርታ አዲሱን የትግራይ ክልል ክለቦች ደንብን ተከትሎ አስፈርሟል፡፡

ትዕግስት ዘውዴ ክለቡን በይፋ ተቀላቅላች ፈጣኗ የቀድሞው የደደቢት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የመስመር አጥቂዋ እስከ ውድድር ዘመን መጨረሻ ድረስ በአቃቂ ለመቆየት ተስማምታለች፡፡ ሁለተኛዋ ፈራሚ ዮርዳኖስ በርሄ ነች። በቀኝ መስመር አጥቂነቷ በመቐለ ተስፋ ሰጪ ቆይታ የነበራት ተጫዋቿ አቃቂን እንደ ትዕግስት ሁሉ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ለማገልገል ፊርማዋን አኑራለች፡፡

እስካሁን በአንደኛ ዲቪዚዮን ውድድር ላይ በስድስት የሊግ መርሀ ግብሮች ሁለት ነጥብ ብቻ ይዞ መጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኘው ክለቡ በቀጣይ ምን አይነት ቅርፅ ይዞ ብቅ ይላል የሚለው ተጠባቂው ጉዳይ ነው፡፡

ከሴቶች ፕሪምየር ሊግ ጋር በተያያዘ ድሬዳዋ ከተማ ከቀናት በፊት ከመቐለ 70 እንደርታ ብርሀን ኃይለሥላሴ፣ ፍሬወይኒ አበራ እና ትንቢት ሳሙኤል ማስፈረማቸው የሚታወስ ሲሆን አዳማ ከተማም በተመሳሳይ ከመቐለ ሔለን እሸቱ እና ቅድስት ቦጋለን ወደ ቡድኑ ከሰሞኑ ቀላቅለዋል። አዲስ አበባ ከተማ አክበረት ገብረፃድቅን፣ ኤሌክትሪክ ዮርዳኖስ ምዑዝን ማስፈረም ችለዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ