ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | የንግድ ባንክ እና መከላከያ ጨዋታ የዲሲፕሊን ውሳኔ ተሰጠበት

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አምስተኛ ሳምንት በንግድ ባንክ እና መከላከያ መካከል የተደረገው ጨዋታ መቋረጡ ይታወሳል። ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በመከላከያ ላይ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ጨዋታው 1-1 ሆኖ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት ሎዛ አበራ ከቅጣት ምት ወደ ጎል የላከችውን ኳስ ዋና ዳኛዋ ከረዳት ዳኛዋ ጋር በመነጋገር ጎል ሆና የፀደቀች ሲሆን መከላከያዎች ኳሷ ከግቡ መስመር አላለፈችም በማለት ተቃውሟቸውን በማሰማት ሜዳውን ለቀው መውጣተቸው ይታወሳል። በዕለቱ የተቀረፀ ቪድዮን በማስረጃነት በመያዝም ለዕለቱ ኮሚሽነር ክስ ማስመዝገባቸው ይታወቃል።

ፌዴሬሽኑ በክስተቱ ዙርያ የነበሩ ጉዳዮችን ተመልክቶ ውሳኔ ያስተላፈ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ እነዚህን ይመስላሉ:-

– ጨዋታውን አቋርጠው በመውጣታቸው መከላከያ የፎርፌ ተሸናፊ ሆኖ ለተጋጣሚው ንግድ ባንክ ሦስት ነጥብ እና ሦስት ጎል እንዲሰጥ

– ጨዋታውን አቋርጠው በመውጣታቸው ከፎርፌ በተጨማሪ 100,000 ብር ቅጣት ተጥሎባቸዋል።

– የመከላከያ ቡድን ዳኛን የማዋከብ ድርጊት የኮቪቭ ፕሮቶኮልን የጣሰ በመሆኑ 10,000 ብረሰ ቅጣት

– ሻለቃ መልካሙ ዘሪሁን ቡድኑን አረጋግተው ወደ ሜዳ መመለስ ሲገባቸው ይህን ባለማድረጋቸው የስድስት ወር እገዳ እና 10,000 ቅጣት ተላልፎባቸዋል።

– በመከላከያ በኩል የቀረበው የቪድዮ ማስረጃ ከአንድ አቅጣጫ ብቻ የሚያመለክት በመሆኑ ውድቅ ተደርጓል።

ሙሉ ውሳኔው ይህን ይመስላል:-

© ሶከር ኢትዮጵያ