ሲዳማ ቡና ከ ድሬዳዋ ከተማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

09፡00 ሲሆን በሚጀምረው ጨዋታ ሲዳማ እና ድሬዳዋ የሚጠቀሟቸው ተጫዋቾች ታውቀዋል።

አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ በፋሲል ከነማ ከተሸነፈው ስብስብ የሦስት ተጫዋቾች ለውጥን አድርገዋል። በዚህም በተከላካይ ስፍራ ሰንዴይ ሙቱኩ በላውረንስ ኤድዋርድ ምትክ ሲሰለፍ ማማዱ ሲዲቤ ከግል ጉዳይ መልስ በእሱባለው ሙሉጌታ ምትክ ወደ አሰላለፉ ተመልሷል። ተመስገኝ በጅሮንድም የአማኑኤል እንዳለን ቦታ ተክቶ በመጀመርያ አሰላለፍ የገባ ተጫዋች ነው።

የአሰልጣኝ ፍሰሀ ጥዑመልሳኑ ድሬዳዋ ከተማም በባህር ዳር ከተማ ከተሸነፈበት ጨዋታ በተመሳሳይ ሦስት ለውጦችን አድርጓል። በዚህም ከጉዳት የተመለሱት ምንያምር ጴጥሮስ እና ሱራፌል ጌታቸው እንዲሁም በወረቀት ጉዳዮች ምክንያት ያልነበረው ጁንያስ ናንጄቦ ወደ ሜዳ ሲመለሱ ያሬድ ዘውድነህ ፣ ሪችሞን ኦዶንጎ እና ፍሬዘር ካሳ ወደ ተጠባባቂነት ወርደዋል።

የቡድኖቹ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ሲዳማ ቡና

30 መሳይ አያኖ
17 ዮናታን ፍሰሀ
2 ፈቱዲን ጀማል
32 ሰንዴይ ሙቱኩ
12 ግሩም አሰፋ
16 ብርሀኑ አሻሞ
10 ዳዊት ተፈራ
29 ያስር ሙገርዋ
15 ተመስገን በጅሮንድ
9 ሀብታሙ ገዛኸኝ
27 ማማዱ ሲዲቤ

ድሬዳዋ ከተማ

30 ፍሬው ጌታሁን
16 ምንያምር ጴጥሮስ
6 ፍቃዱ ደነቀ
15 በረከት ሳሙኤል
4 ሄኖክ ኢሳይያስ
5 ዳንኤል ደምሴ
8 ሱራፌል ጌታቸው
9 ኤልያስ ማሞ
17 አስቻለው ግርማ
99 ሙኅዲን ሙሳ
20 ጆንያስ ናንጄቦ


© ሶከር ኢትዮጵያ