ወልቂጤ ከተማ አጥቂ አስፈርሟል

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ባወጣው ልዩ የዝውውር ደንብ መሠረት ወልቂጤ ከተማ አጥቂ አስፈርሟል።

የመቐለ 70 እንደርታው ያሬድ ከበደ የሠራተኞቹ አዲስ ፈራሚ ነው። መቐለ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ብሎም የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ ግንባር ቀደም ሚና ከተጫወቱ ተጫዋቾች አንዱ የነበረው ያሬድ በክረምቱ በክለቡ ቆይታውን ማራዘሙ የሚታወስ ቢሆንም የትግራይ ክልል ክለቦች ዘንድሮ በሊጉ ላይ የማይሳተፉ በመሆናቸውና ተጫዋቾቹ ለዚህ ዓመት ወደፈለጉበት ክለብ እንዲያመሩ በወጣው አዲስ ደንብ መሠረት ወደ ወልቂጤ አምርቷል።

ያሬድ በወልቂጤ የመቐለ የቡድን ጓደኞቹ አሚን ነስሩ እና ሥዩም ተስፋዬን የሚያገኝ ሲሆን ክፍተት ለታየበት የቡድኑ የአጥቂ ክፍል ጥሩ አማራጭ እንደሚሆን ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ