ባህር ዳር ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዛሬ ረፋዱ ጨዋታ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

በሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ ስር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምክትል የነበሩት ብሎም በአምበልነት የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ያነሱ ሁለት አሰልጣኞችን የሚያገናኘው ጨዋታ ከደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል።

የአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኙ ባህር ዳር ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 1-0 የሻነፈበትን የተጫዋቾች ምርጫ ዛሬም በመጠቀም ወደ ሜዳ ይገባል። በተመሳሳይ አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት በከፍተኛ የጨዋታ ብልጫ ወላይታ ድቻ ላይ ድል ያስገኘላቸውን የመጀመሪያ አሰላለፍ መቀየር አልፈለጉም። በዚህም ሁለቱም ቡድኖች የስድስተኛው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ቀዳሚ ስብስባቸውን ሙሉ ለሙሉ በሰባተኛው ሳምንት መጀመሪያ ላይም ተጠቅመዋል።

በጨዋታው ምንይሉ ወንድሙ እና ወሰኑ ዓሊ ከፋሲል ጋር በነበረው ጨዋታ በተመለከቱት ሁለተኛ ቢጫ ከነበረባቸው ቅጣት ፣ ሳምሶን ጥላሁን ደግሞ ለሦስት የጨዋታ ሳምንታት ከሜዳ ካራቀው ጉዳት መልስ ተጠባባቂ ወንበር ላይ ተቀምጠዋል። በሀዋሳ በኩልም ተከላካይ አማካዩ ጂብሪል አህመድ በሥራ ፍቃድ አለመታደስ ምክንያት ካመለጠው የድቻው ጨዋታ መልስ ተጠባባቂ ሆኗል።

ጨዋታው በፌዴራል ዳኛ አዳነ ወርቁ የሚመራ ይሆናል።

የቡድኖቹ የመጀመሪያ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ባህር ዳር ከተማ

99 ሀሪስተን ሄሱ
3 ሚኪያስ ግርማ
15 ሰለሞን ወዴሳ
6 መናፍ ዐወል
18 ሳላምላክ ተገኝ
21 ፍቅረሚካኤል ዓለሙ
24 አፈወርቅ ኃይሉ
13 አህመድ ረሺድ
7 ግርማ ዲሳሳ
14 ፍጹም ዓለሙ
9 ባዬ ገዛኸኝ

ሀዋሳ ከተማ

1 ሜንሳህ ሶሆሆ
7 ዳንኤል ደርቤ
16 ወንድምአገኝ ማዕረግ
4 ምኞት ደበበ
26 ላውረንስ ላርቴ
12 ደስታ ዮሐንስ
18 ዳዊት ታደሰ
3 ኤፍሬም ዘካርያስ
29 ወንድማገኝ ኃይሉ
17 ብሩክ በየነ
10 መስፍን ታፈሰ


© ሶከር ኢትዮጵያ