ለብሔራዊ ቡድን ዝግጅት 28 ተጫዋቾች ጥሪ ቀረበላቸው

ከሁለት ወራት በኋላ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በጅማ ለሚያርደርገው ዝጅግት ሃያ ስምንት ተጫዋቾች ተጠርተዋል።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ባደረጉት ጥሪ አመዛኞቹ ተጫዋቾች ከዚህ ቀደም ከኒጀር ባደረጉት ጨዋታ የተጠቀሙባቸው ሲሆኑ ጥሩ አቋም ላይ የሚገኙት ፍሬው ጌታሁን፣ ፋሲል ገብረሚካኤል፣ ኤልያስ አታሮ፣ ቶማስ ስምረቱ እና አብዱልከሪም ወርቁን የመሳሰሉ አዳዲስ ፊቶች ተካተዋል። ኤልያስ ማሞ እና ዳዋ ሆሄሳ ደግሞ ከረጅም ጊዜ በኋላ ወደ ስብስቡ የተጠሩ ተጫዋች ናቸው።

ከኒጀሩ ጨዋታ ስብስብ እንደ አዲስ ግደይ፣ ከነዓን ማርክነህ፣ አቤል ማሞ፣ ይሁን እንደሻው፣ አማኑኤል ዮሐንስ እና ሱራፌል ዳኛቸውን የመሳሰሉ ተጫዋቾች ያልተካተቱ ተጫዋቾች ናቸው። 

ጥሪ የተደረላቸው ተጫዋቾች ከትናንት ጀምሮ መገኘታቸውን ሪፖርት እያረጉ ሲሆን በነገው ዕለት የመጨረሻ የማምረጊያ ቀን መሆኑንና ከሰዓት ልምምዳቸውን ጅማ ላይ እንደሚጀምሩ ሰምተናል። እስከ ረቡዕ ልምምድ እንደሚያርጉ የታወቀ ሲሆን የፕሪምየር ሊጉ ውድድር ለአንድ ወር በጅማ የሚከናወን በመሆኑ በየመሐሉ ክፍት ጊዜ ሲኖር እየተሰበሰቡ ልምምድ ማድረግ እንደሚቀጥሉ ታውቋል።

ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች

ተክለማርያም ሻንቆ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ጀማል ጣሰው (ወልቂጤ)፣ ፍሬው ጌታሁን (ድሬዳዋ)፣ ፋሲል ገብረሚካኤል (ሰበታ ከተማ)

ተከላካዮች

ሱሌይማን ሀሚድ (ሀዲያ ሆሳዕና)፣ አሥራት ቱንጆ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ አስቻለው ታመነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ያሬድ ባየህ (ፋሲህ ከነማ)፣ ቶማስ ስምረቱ (ወልቂጤ ከተማ)፣ ወንድሜነህ ደረጄ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ኤልያስ አታሮ (ጅማ አባ ጅፋር)፣ ረመዳን የሱፍ (ወልቂጤ ከተማ)፣ አምሳሉ ጥላሁን (ፋሲል ከነማ)

አማካዮች

ታፈሰ ሰለሞን (ኢትዮጵያ ቡና)፣ መስዑድ መሐመድ (ሰበታ ከተማ)፣ አብዱልከሪም ወርቁ (ወልቂጤ ከተማ)፣ ሀብታሙ ተከስተ (ፋሲል ከነማ)፣ ኤልያስ ማሞ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ሀይደር ሸረፋ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ፍፁም ዓለሙ (ባህር ዳር ከተማ)፣ ጋዲሳ መብራቴ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሽመክት ጉግሳ (ፋሲል ከነማ)

አጥቂዎች

ጌታነህ ከበደ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ አቤል ያለው (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ አቡበከር ናስር (ኢትዮጵያ ቡና)፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ዳዋ ሆቴሳ (ሀዲያ ሆሳዕና)፣ ሙጂብ ቃሲም (ፋሲል ከነማ)


© ሶከር ኢትዮጵያ