ሀዲያ ሆሳዕና አማካይ አስፈርሟል

የፕሪምየር ሊጉ መሪ ሀዲያ ሆሳዕና የልዩ ዝውውር ደንብን ተጠቅሞ የአጥቂ አማካይ አስፈርሟል።

የመቐለ 70 እንደርታው አማካይ ዮናስ ገረመው የአሸናፊ በቀለን ስብስብ የተቀላቀለ ተጫዋች ነው። የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና፣ ንግድ ባንክ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ጅማ አባ ጅፋር አማካይ በጅማ እና መቐለ ለተከታታይ ዓመታት የሊጉን ዋንጫ ያነሳ ሲሆን በትግራይ ክልል የሚጫወቱ ተጫዋቾች ለዚህ ዓመት ወደ ሌሎች ክለቦች አምርተው እንዲጫወቱ በወጣው ልዩ የዝውውር ደንብ መሠረት ሀዲያ ሆሳዕናን መቀላቀል ችሏል።

ዝውውሩን ተከትሎ በተለያዩ የአማካይ ክፍል ሚናዎች መጫወት የሚችለው ዮናስ ለአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ተጨማሪ የማጥቃት ኃይል እንደሚሆን ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ