የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ወደ ካሜሩን አቅንተዋል

በካሜሮን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የቻን ውድድር እና ተዛማጅ ጉዳዮች የፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ ለሳምንታት ቆይታ ወደ ካሜሩን አቅንተዋል።

በሀገር ውስጥ ሊጎች ተጫዋቾች ብቻ የሚካሄደው የቻን ውድድር በኮሮና ሻይረስ ምክንያት በ2020 መካሄድ ሲገባው ተገፍቶ ከቀናት በኋላ በካሜሩን አስተናጋጅነት እንደሚካሄድ ይታወቃል። በዚህ ውድድር በክብር እንግድነት ተጋብዘው ፕሬዝደንት ኢሳያስ ጅራ በትናትናው ዕለት ወደ ካሜሩን አቅንተዋል። ለአንድ ወር በሀገሪቱ ቆይታ የሚያደርጉት ፕሬዝዳንቱ እግረ መንገዳቸውን የካፍ ዓመታዊ ጠቃላላ ጉባዔ ላይ እንደሚካፈሉ ተሰምቷል። ካፍ በዘንድሮ ጠቅላላ ጉባዔው ላይ አዲስ ፕሬዝዳንት ይመርጣል ተብሎም ይጠበቃል።

በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ብቸኛዋ ሴት ዋና ዳኛ ኢትዮጵያዊቷ ሊዲያ ታፈሰ ውድድሩን ለመምራት ባሳለፍነው ቅዳሜ ወደ ሥፍራው ማቅናቷ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ