ጅማ አባ ጅፋር ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

የሰባተኛው ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ-ግብር የሆነው የጅማ አባ ጅፋር እና ቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ ታውቋል።

የአሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ቡድን ከሰበታ ከተማ ጋር ነጥብ ከተጋራው የመጀመሪያ አሰላለፉ ውስጥ የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ አድርጓል። በዚህም ከአምስት የጨዋታ ሳምንታት በኋላ ከድር ኸይረዲንን ወደ መጀመሪያ አሰላለፍ ሲመልስ ብዙአየሁ እንዳሻውም በፊት አጥቂነት የሚጀምር ይሆናል። ሁለቱ ተጫዋቾች ተመስገን ደረሰ እና ሳዲቅ ሴቾን በመተካት ነው በአሰላለፉ ውስጥ የተካተቱት።

በሸገር ደርቢ የቀይ ካርድ ሰለባ የሆነው ፓትሪክ ማታሲን በለዓለም ብርሀኑ የተኩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች አማካይ ክፍላቸው ላይ ባደረጉት ሌላኛው ለውጥ የአብስራ ተስፋዬ በሀይደር ሸረፋ ምትክ ጨዋታውን ጀምሯል። የአብስራ በዚህ የውድድር ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በቀዳሚው አሰላለፍ ውስጥ ተካቷል።

የቡድኖቹ የዛሬው አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ጅማ አባ ጅፋር

1 ጄኮ ፔንዜ
2 ወንድምአገኝ ማርቆስ
16 መላኩ ወልዴ
4 ከድር ኸይረዲን
14 ኤልያስ አታሮ
21 ንጋቱ ገብረሥላሴ
8 ሱራፌል አወል
22 ሳምሶን ቆልቻ
10 ሙሉቀን ታሪኩ
27 ሮባ ወርቁ
17 ብዙአየሁ እንዳሻው

ቅዱስ ጊዮርጊስ

1 ለዓለም ብርሀኑ
14 ሄኖክ አዱኛ
15 አስቻለው ታመነ
23 ምንተስኖት አዳነ
24 ኤድዊን ፍሪምፖንግ
16 የአብስራ ተስፋዬ
20 ሙሉዓለም መስፍን
27 ሮቢን ንጋላንዴ
11 ጋዲሳ መብራቴ
10 አቤል ያለው
9 ጌታነህ ከበደ


© ሶከር ኢትዮጵያ