ወላይታ ድቻ ከ ሰበታ ከተማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

ከደቂቃዎች በኃላ የሚጀምረው የድቻ እና የሰበታ ጨዋታ የመጀመሪያ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ወላይታ ድቻ አዲስ አበባ ላይ ካደረገው የመጨረሻ ጨዋታ የሦስት ተጫዋቾች ለውጥ አድርጓል። በዚህም ግብ ጠባቂው ሲዒድ ሀብታሙ በመክብብ ደገፉ ሲተካ ከጉዳት የተመለሰው ደጉ ደበባ እና እንድሪስ ሰዒድም በአማኑኤል ተሾመ እና ቸርነት ጉግሳ ምትክ ወደ መጀመሪያ አሰላለፍ መጥተዋል። ቡድኑ የአዲሱ አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው የወረቀት ጉዳዮች ባለመጠናቀቃቸው በግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ዘላለም ማቴዎስ የሚመራም ይሆናል። አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው በተመልካች መቀመጫ ላይ ተሰይመውም ታይተዋል።

አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ ቡድናቸው ከጅማ አባ ጅፋር ጋር ነጥብ ከተጋረራበት ጨዋታ ሦስት ማስተካከያዎች አድርገዋል። ግብ ጠባቂው ፋሲል ገብረሚካኤልን በምንተስኖት አሎ ቦታ ተጠቅመው ስድስተኛው ሳምንት ላይ ያጣውን ቀዳሚ ተመራጭነት ሲመልሱለት ለመጀመሪያ ጊዜ ዳዊት እስጢፋኖስን ተጠባባቂ አድርገው ዳንኤል ኃይሉን ለመጀመርያ ጊዜ አማካይ ክፍል ላይ ተጠቅመዋል። ከዚህ በተጨማሪ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰለፈው አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ ተጠባባቂ ተደርጎ ዝውውሩ በቅርቡ የፀደቀለት አብዱልባስጥ ከማል በቀዳሚው አሰላለፍ ውስጥ ተካቷል።

የቡድኖቹ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ወላይታ ድቻ

99 መክብብ ደገፉ
9 ያሬድ ዳዊት
12 ደጉ ደበበ
26 አንተነህ ጉግሳ
16 አናጋው ባደግ
15 መልካሙ ቦጋለ
20 በረከት ወልዴ
8 እንድሪስ ሰዒድ
6 ኤልያስ አህመድ
4 ፀጋዬ ብርሀኑ
11 ያሬድ ዳርዛ

ሰበታ ከተማ

44 ፋሲል ገብረሚካኤል
5 ጌቱ ኃይለማርያም
4 አንተነህ ተስፋዬ
12 ቢያድግልኝ ኤልያስ
24 ያሬድ ሀሰን
29 አብዱልባስጥ ከማል
6 ዳንኤል ኃይሉ
17 ታደለ መንገሻ
3 መስዑድ መሐመድ
8 ፉአድ ፈረጃ
19 እስራኤል እሸቱ


© ሶከር ኢትዮጵያ