የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች ላይ የቀን ሽግሽግ ተደርጓል

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቀጣይ መርሐ ግብር ላይ መጠነኛ የቀን ሽግሽግ ተደርጓል።

ውድድሩ በሁለተኛ አስተናጋጅ ከተማ ጅማ ቀጥሎ እየተካሄደ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን አስቀድሞ በወጣው መርሐ ግብር ላይ በ10ኛ እና 11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች መካከል የአራት ቀናት ክፍተት የነበረ በመሆኑ ይህን ክፍተት በማጥበብ በ11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ ቀን ሽግሽግ ተደርጓል።

ለውጡ ይህንን ይመስላል:-

ቀድሞ አዲስ
ሲዳማ ከ ቡና ጥር 28 ጥር 26
ሆሳዕና ከ ጊዮርጊስ ጥር 29 ጥር 26
ባህር ዳር ከ ጅማ ጥር 28 ጥር 27
አዳማ ከ ሰበታ ጥር 29 ጥር 27
ወልቂጤ ከ ሀዋሳ ጥር 30 ጥር 28
ፋሲል ከ ድሬዳዋ ጥር 30 ጥር 28

 


© ሶከር ኢትዮጵያ