የሸገር ደርቢ የሚካሄድበት ከተማ ታውቋል

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛው ዙር ተጠባቂውን የሸገር ደርቢ ጨዋታ የምታስተናግደው ከተማ እና ቀን ታውቋል።

ከረጅም ዓመታት ወዲህ ተጠባቂነቱን የሚመጥን የደርቢ ጨዋታ የተመለከትንበት የዘንድሮው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ በርካታ አነጋጋሲ ክስተቶች አስተናግዶ እና በአስር ዓመታት ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ ከሦስት በላይ ጎል ተቆጥሮበት በኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወቃል።

ከወዲሁ ሁለተኛውን ዙርን ተናፋቂ ያደረገው
ይህ ጨዋታ ከሦስት ወር በኃላ በአስራ ዘጠነኛው ሳምንት በዕለተ ማክሰኞ ሚያዚያ 5 ቀን 9:00 ላይ በምስራቃዊቷ ከተማ ድሬዳዋ እንዲካሄድ መርሐግብር ወጥቶለታል።

ሶከር ኢትዮጵያ ከቀናት በኋላ አጠቃላይ የውድድር መርሐግብሮችን ዝርዝር ውድድሩን ከሚያዘጋጁ ከተሞች ጋር በማድረግ ለአንባቢያን እንደምታደርስ ከወዲሁ ትገልፃለች።


© ሶከር ኢትዮጵያ