ሀዲያ ሆሳዕና ከ ፋሲል ከነማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

04፡00 ላይ ለሚጀምረው ተጠባቂ ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች የመረጡት የመጀመሪያ አሰላለፍ የታወቀ ሲሆን ያልተጠበቁ ለውጦችም ተደርገዋል።
በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመራው ሀዲያ ሆሳዕና ለመጀመሪያ ጊዜ ነጥብ በጣለበት የወልቂጤው ጨዋታ ከተጠቀመበት አሰላለፍ ውስጥ ሦስት ለውጦች አድርጓል። ባልተጠበቁት ሁለት ለውጦች የፊት አጥቂዎቹ ሳሊፉ ፎፋና እና ቢስማርክ አፒያ በቴዎድሮስ በቀለ እና ሚካኤል ጄርጅ ተተክተዋል። ሚካኤል በዚህ የውድድር ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በቀዳሚው አሰላለፍ ውስጥ ተካቷል። ሦስተኛው የቡድኑ ለውጥ ዱላ ሙላቱ ካሉሻ አልሀሰን የተተካበት ሆኗል።

አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ከጨዋታው በፊት እንደተናገሩት ቡድኑ በምግብ መመረዝ ሳቢያ ስድስት ተጫዋቾቹን መጠቀም እንዳልቻለ ጠቁመዋል።

ፋሲል ከነማ ሲዳማ ቡናን ማሸነፍ በቻለበት የስድስተኛው ሳምንት ጨዋታ ከባድ ጉዳት አስተናግዶ ከሜዳ ወጥቶ የቀዶ ጥገና ያደረገው ሰዒድ ሁሴንን ቦታ በእንየው ካሳሁን በመተካት ቀሪው ስብስቡ ላይ ለውጥ ሳያደርግ ጨዋታውን ይጀምራል።

የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ሀዲያ ሆሳዕና

32 ደረጄ ዓለሙ
2 ሱሌይማን ሀሚድ
5 አይዛክ ኢሴንዴ
25 ተስፋዬ በቀለ
3 ቴዎድሮስ በቀለ
17 ሄኖክ አርፊጮ
21 ተስፋዬ አለባቸው
10 አማኑኤል ጎበና
13 ካሉሻ አልሀሰን
12 ዳዋ ሆቴሳ
11 ሚካኤል ጆርጅ

ፋሲል ከነማ

1 ሚኬል ሳማኬ
2 እንየው ካሳሁን
5 ከድር ኩሊባሊ
16 ያሬድ ባየህ
21 አምሳሉ ጥላሁን
14 ሀብታሙ ተከስተ
8 ይሁን እንደሻው
10 ሱራፌል ዳኛቸው
12 ሳሙኤል ዮሐንስ
19 ሽመክት ጉግሳ
26 ሙጂብ ቃሲም


© ሶከር ኢትዮጵያ