ሰበታ ከተማ ከ ባህር ዳር ከተማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

የስምንተኛው ሳምንት ቀዳሚ መርሐ-ግብር ከደቂቃዎች በኋላ ሲጀምር በርካታ ለውጦች የተደረጉበት የቡድኖቹ የመጀመሪያ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።

ከወላይታ ድቻ ጋር በነበረው የሰባተኛ ሳምንት ጨዋታ ሦስት የሚደርሱ ተጫዋቾቻቸው የተጎዱባቸው ሰበታዎች ዛሬ በተመሳሳይ ሦስት ለውጦች አድርገዋል። ቡድኑ ፍፁም ገብረማርያም እና ቡልቻ ሹራን በእስራኤል እሸቱ እና ታደለ መንገሻ ምትክ ወደ መጀመሪያ አሰላለፍ ሲመልስ መሳይ ጻውሎስም በቢያድግልኝ ኤልያስ ቦታ ተተክቷል።

ከወትሮው በተለየ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ በሀዋሳ 2-1 ሲረቱ ከተጠቀሙበት ጨዋታ የአምስት ተጫዋቼች ለውጥ አድርገዋል በዢህም ሀሪሰን ሄሱ ፣ ሚኪያስ ግርማ ፣ አፋወርቅ ኃይሉ ፣ ግርማ ዲሳሳ እና ባዬ ገዛኸኝ በፂዮን መርዕድ ፣ ሳሙኤል ተስፋዬ ፣ ሳምሶን ጥላሁን ፣ ወሰነ ዓሊ እና ምንይሉ ወንድሙ ወደ መጀመሪያ አሰላለፍ መጥተዋል።

በዚህም ሳምሶን ጥላሁን ከሳምንታት ጉዳት በኋላ ሲመለስ ፂዮን መርዕድ ፣ ምንይሉ ወንድሙ እና ሳሙኤል ተስፋዬ ለመጀመሪያ ጊዜ በቀዳሚ አሰላለፍ ውስጥ ተካተዋል።

የሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ሰበት ከተማ

44 ፋሲል ገብረሚካኤል
5 ጌቱ ኃይለማርያም
4 አንተነህ ተስፋዬ
13 መሳይ ጳውሎስ
24 ያሬድ ሀሰን
29 አብዱልባስጥ ከማል
6 ዳንኤል ኃይሉ
3 መስዑድ መሐመድ
8 ፉአድ ፈረጃ
16 ፍፁም ገብረማርያም
7 ቡልቻ ሹራ

ባህር ዳር ከተማ

22 ጽዮን መርዕድ
16 ሳሙኤል ተስፋዬ
15 ሰለሞን ወዴሳ
6 መናፍ ዐወል
13 አህመድ ረሺድ
18 ሳላምላክ ተገኝ
8 ሳምሶን ጥላሁን
21 ፍቅረሚካኤል ዓለሙ
14 ፍጹም ዓለሙ
10 ወሰኑ ዓሊ
25 ምንይሉ ወንድሙ


© ሶከር ኢትዮጵያ