09፡00 ላይ በሚጀምረው የጊዮርጊስ እና የድቻ ጨዋታ ቡድኖቹ ወደ ሜዳ ይዘውት የሚገቡት አሰላለፍ እና የተደረጉ ለውጦችን እነሆ።
አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስ ከእስካሁኑ ሳምንታት በትከት ያሉ ለውጦች አድርገዋል። በዚህም ጅማ አባ ጅፋርን ከረቱበት ጨዋታ ምንተስኖት አዳነ ፣ ሙሉዓለም መስፍን ፣ ሮቢን ንግላንዴን በአማኑኤል ትርፋ ፣ ሀይደር ሸረፋ እና አማኑኤል ገብረሚካኤል ለውጠዋል። በዚህም ሁለቱ አማኑኤሎች ለመጀመሪያ ጊዜ በቀዳሚው አሰላለፍ ውስጥ ተካተዋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው እየተመራ ወደ ሜዳ የገባው ወላይታ ድቻ ባደረገው ብቸኛ ለውጥ ያሬድ ዳርዛ በቢኒያም ፍቅሬ የተቀየረ ሲሆን ከሰበታ ጋር አቻ የተለያየው ቀሪ ስብስብ በድጋሚ ጥቅም ላይ ውሏል። ቢኒያም የዓመቱን የመጀመሪያ ጨዋታውን በቀዳሚ ተሰላፊነት ያደርጋል።
የቡድኖቹ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል
ቅዱስ ጊዮርጊስ
1 ለዓለም ብርሀኑ
14 ሄኖክ አዱኛ
15 አስቻለው ታመነ
24 ኤድዊን ፍሪምፖንግ
3 አማኑኤል ትርፋ
16 የአብስራ ተስፋዬ
5 ሀይደር ሸረፋ
11 ጋዲሳ መብራቴ
10 አቤል ያለው
28 አማኑኤል ገብረሚካኤል
9 ጌታነህ ከበደ
ወላይታ ድቻ
99 መክብብ ደገፉ
9 ያሬድ ዳዊት
12 ደጉ ደበበ
26 አንተነህ ጉግሳ
16 አናጋው ባደግ
15 መልካሙ ቦጋለ
20 በረከት ወልዴ
8 እንድሪስ ሰዒድ
6 ኤልያስ አህመድ
4 ፀጋዬ ብርሀኑ
13 ቢኒያም ፍቅሬ
© ሶከር ኢትዮጵያ