“ደስታዬን በዛ መንገድ የገለፅኩት…” – ግርማ ዲሳሳ

ግርማ ዲሳሳ ዛሬ ግብ ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን ስለገለፀበት መንገድ ነግሮናል። 

በዛሬ ጠዋቱ የሰበታ ከተማ እና የባህርዳር ከተማ ጨዋታ ላይ ተቀይሮ በመግባት ቡድኑ ያጣውን የጨዋታ ብልጫ እንዲያገኝ የበከሉን ያደረገው ግርማ ዲሳሳ በፍፁም ቅጣት ምት ግብ ማስቆጠርም ችሏል። የመስመር አማካዩ ግቧን ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን የገለፀበት የተለየ መንገድ ደግሞ ትኩረት የሚስብ ነበር። ጉዳዩን አስመልክተን ለተጫዋቹ ላቀረብንለት ጥያቄ ተከታዩን ምላሽ ሰጥቶናል።

” ደስታዬን በዛ መንገድ የገለፅኩበት ምክንያት ባለቤቴ ነፍሰጡር በመሆኗ ነው። ደስታዬን የምገልፅበትን መንገድ ለማሳየት ጉጉቱ ነበረኝ። በመጨረሻም ጎል ማስቆጠሬ ጥሩ አጋጣሚ ስለፈጠረልኝ በሷ ደስተኛ መሆኔን ለማሳየት ተጠቅሜበታለሁ። ምንያህል እንደምወዳት እና እንደማስባት እንድታውቅ ነው በዛው አጋጣሚ። ”


© ሶከር ኢትዮጵያ