የያሬድ ከበደ ወደ ወልቂጤ ዝውውር እክል አጋጥሞታል

የመቐለ 70 እንደርታው ያሬድ ከበደ የሠራተኞቹ አዲስ ፈራሚ ለመሆን ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም ዝውውሩ እክል አጋጥሞታል።

መቐለ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲያድግ ብሎም የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ ግንባር ቀደም ሚና ከተጫወቱ ተጫዋቾች አንዱ የነበረው ያሬድ የትግራይ ክልል ክለቦች ዘንድሮ በሊጉ ላይ የማይሳተፉ በመሆናቸውና ተከትቶ ፌዴሬሽኑ ባዘጋጀው ልዩ የተጫዋቾች ዝውውር መመርያ ተጠቃሚ በመሆን በቅርቡ ወደ ወልቂጤ አምርቶ እንደነበረ ይታወቃል።
ሆኖም ከስምምነት የደረሱበት ጉዳይ ተፈፃሚ ሊሆን እንዳልቻለ በማሰብ በሁለቱም መካከል የነበረው ስምምነት ሳይፀድቅ በመቅረቱ ተጫዋቹ ወደ ትውልድ ከተማው መቐለ ዳግም መመለሱን ለማወቅ ችለናል። ያሬድ ምናልባት አንደኛው ዙር ሲጠናቀቅ ወደ ሌላ ክለብ ሊያመራ እንደሚችል ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ