ድሬዳዋ ከተማ ከ ሀዲያ ሆሳዕና – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

04፡00 ሲል የሚጀምረው የዕለቱ የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ ቡድኖች በዚህ አሰላለፍ ወደ ሜዳ ይገባሉ።

ሀዲያ ሆሳዕና ፋሲል ከነማ የመጀመሪያው ሽንፈት ሲገጥመው ከተጠቀመው ቡድን ውስጥ ከህመም የተመለሱለትን ጨምሮ ሦስት ተጫዋቾችን ለውጧል። በዚህም ካሉሻ አልሀሰን ፣ ሚካኤል ጆርጅ እና ተስፋዬ በቀለ ወጥተው አዲስ ህንፃ ፣ ቢስማርክ አፒያ እና ሳሊፉ ፎፋና ገብተዋል።

በሲዳማ ሽንፈት ባስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በኩል ጉዳት በመበርከቱ የተነሳ ይመስላል በርከት ያሉ ለውጦች ተደርገዋል። በዚህም ዘነበ ከበደ፣ ፍሬዘር ካሣ፣ ኩዌኩ አንዶህ እና አስጨናቂ ሉቃስ ገብተው ፍቃዱ ደነቀ፣ በረከት ሳሙኤል፣ ሄኖክ ኢሳይያስ እና ሱራፌል ጌታቸው አርፈዋል።

የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ድሬዳዋ ከተማ

30 ፍሬው ጌታሁን
2 ዘነበ ከበደ
21 ፍሬዘር ካሣ
12 ኩዌኩ አንዶህ
27 አስጨናቂ ሉቃስ
16 ምንያምር ጴጥሮስ
5 ዳንኤል ደምሴ
9 ኤልያስ ማሞ
17 አስቻለው ግርማ
99 ሙኅዲን ሙሳ
20 ጁንያስ ናንጄቦ

ሀዲያ ሆሳዕና

32 ደረጄ ዓለሙ
2 ሱሌይማን ሀሚድ
5 አይዛክ ኢሴንዴ
3 ቴዎድሮስ በቀለ
17 ሄኖክ አርፊጮ
23 አዲስ ህንፃ
21 ተስፋዬ አለባቸው
10 አማኑኤል ጎበና
22 ቢስማርክ አፒያ
20 ሳሊፉ ፎፋና
12 ዳዋ ሆቴሳ


© ሶከር ኢትዮጵያ