ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ስምንተኛ ሳምንት ቁጥሮች እና ዕውነታዎች

በስምንተኛ ሳምንት የተከናወኑ ጨዋታዎችን ተመርኩዘን ቁጥሮች እና ዕውነታዎችን በዚህ መልኩ አሰናድተናል። 

– በዚህ ሳምንት ስድስት ጨዋታዎች ተደርገው 17 ጎሎች ተቆጥረዋል። በአማካይ በጨዋታ 2.9 የተቆጠረበት ይህ ሳምንት ካለፈው በሦስት የተሻለ ነው።

– ባህር ዳር ከተማ እና ፋሲል ከነማ አራት ጎሎች አስቆጥረው ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ ወላይታ ድቻ፣ ሲዳማ ቡና፣ አዳማ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ጎል ሳያስቆጥሩ የወጡ ቡድኖች ናቸው።

– በዚህ ሳምንት ከተቆጠሩ ጎሎች መካከል አራት ጎሎች (ሙጂብ ሁለት፣ ብዙዓየሁ እንደሻው እና ግርማ ዲሳሳ) በፍፁም ቅጣት ምት ሲያስቆጥሩ አንድ ጎል (መስፍን ታፈሰ) ከቆመ የተሻገረ ኳስ አስቆጥሯል። ሌሎች ዘጠኝ ጎሎች የተቆጠሩት በክፍት ጨዋታ ነው።

– ከ17 ጎሎች መካከል አንድ ጎል (ይሁን እንደሻው) ብቻ ከሳጥን ውጪ ሲያስቆጥር ሌሎቹ ጎሎች በሳጥን ውስጥ ተመትተው የተቆጠሩ ናቸው።

– 16 የተለያዩ ተጫዋቾች በዚህ ሳምንት ጎል አስቆጥረዋል። ሙጂብ ቃሲም ሁለት ጎሎች የማስቆጠር ቀዳሚ ሲሆን ሌሎች ተጫዋቾች አንድ አንድ ማስቆጠር ችለዋል።

– ጎል ካስቆጠሩ ተጫዋቾች መካከል አሥራት ቱንጆ፣ ዊልያም ሰለሞን፣ ብዙዓየሁ እንደሻው፣ ሳላዲን ሰዒድ፣ ግርማ ዲሳሳ እና ይሁን እእደሻው በዓመቱ ለመጀመርያ ጊዜያቸው ነው።

– አስር ተጫዋቾች ለጎል በማመቻቸት ተሳትፎ አድርገዋል።

– ጎል በማስቆጠር እና በማመቻቸት ተሳትፎ ያደረጉ ተጫዋቾች ሦስት ናቸው። ዊልያም ሰለሞን፣ ሙጂብ ቃሲም እና ፍፁም ዓለሙ አንድ ጎል እና አንድ አሲስት አስመዝግበዋል። (ፍፁም ዓለሙ ሲያሻግር ያሬድ ሀሰን ጨርፎት የተቆጠረው ጎል በፍፁም ስም ተመዝግቧል።)

– ሙጂብ ቃሲም ስድስተኛ ተከታታይ ጨዋታ ጎል ሲያስቆጥር አቡበከር ናስር እና መስፍን ታፈሰ ሦስተኛ ተከታታይ ጨዋታ ጎላቸውን ማስቆጠር ችለዋል። ሳላምላክ ተገኘ ደግሞ ሁለተኛ ተከታታይ ጎሉን ነው ማስቆጠር የቻለው።

የዲሲፕሊን ቁጥሮች

– በዚህ ሳምንት 17 የማስጠንቀቂያ እና አንድ ቀይ ካርድ (ያሬድ ሀሰን) ተመዟል። ይህም የቀይ ካርድ ካልታየበት ያለፈው ሳምንትም በአራት የማስጠንቀቂያ ካርዶች ያነሰ ነው።

– ሀዲያ ሆሳዕና በስድስት ቢጫ ካርድ ከፍተኛውን ቁጥር ሲይዝ ቡና፣ ፋሲል እና ሲዳማ በአንድ ቢጫ ዝቅተኛውን አስመዝግበዋል።

– በዚህ ሳምንት አምሳሉ ጥላሁን እና እንድሪስ ሰዒድ አራተኛ ቢጫ ካርዳቸውን የተመለከቱ ሲሆን ከሀብታሙ ሸዋለም፣ ሱራፌል ዳኛቸው እና ተስፋዬ አለባቸው ጋር ከፍተኛውን ቁጥር ተጋርተዋል።

የሳምንቱ የጨዋታ ስታቶች

(ቁጥሮቹ የተገኙት ከሱፐር ስፖርት ነው)

ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ

ከፍተኛ – ባህር ዳር ከተማ – 8
ዝቅተኛ – ወላይታ ድቻ – 0

ጥፋቶች

ከፍተኛ – ወላይታ ድቻ እና ሀዲያ ሆሳዕና – 20
ዝቅተኛ – ሰበታ፣ አዳማ እና ቡና – 13

ከጨዋታ ውጪ

ከፍተኛ – ባህርዳር፣ ሲዳማ እና ድሬዳዋ – 6
ዝቅተኛ – ሰበታ፣ ሀዋሳ እና ጅማ – 1

የማዕዘን ምት

ከፍተኛ – ባህር ዳር – 7
ዝቅተኛ – ሀዋሳ እና ሆሳዕና – 1

የኳስ ቁጥጥር ድርሻ

ከፍተኛ – ኢትዮጵያ ቡና – 68%
ዝቅተኛ – ጅማ አባ ጅፋር – 32%


© ሶከር ኢትዮጵያ