የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን የሁለተኛ ዙር ውድድር የት እንደሚደርግ ውሳኔ ተሰጥቶበታል፡፡
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ውድድር የመጀመሪያው ዙር መርሀ ግብር በሀዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ ላይ ከታኃሣሥ 10 ጀምሮ እየተደረገ እነሆ ስምንተኛ ሳምንቱ ላይ ደርሷል፡፡የሁለተኛ ዙር መርሀ ግብር በሀዋሳ ይቀጥል ወይስ በአዳማ ወይንም በአዲስ አበባ ይደረግ በሚሉ ጉዳዮች ላይ በቅርቡ ከክለብ አመራሮች ጋር የሊጉ የውድድር መሪዎች ውይይት ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን በውይይቱም ሳይወሰን መቅረቱ ይታወሳል፡፡ ይሁንና የአዲስ አበባ ስታዲየም በዕድሳት ላይ መሆኑን እና በሀዋሳ እንዳይቀጥል የመጫወቻ ሜዳው ሰው ሰራሽ ሳር በመሆኑ በእነኚህ ከተማዎች ሊደረግ የታሰው ቀርቶ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ከየካቲት 6 ጀምሮ እንዲደረግ ተወስኗል፡፡ በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ውድድር በአዳማ ከተማ የካቲት 6 ጀምሮ እስከ መጋቢት 7 ድረስ በከተማው እየተደረገ የሚቆይ ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዚዮን የሁለተኛ ዙር ጨዋታ በቅርቡ በአዳማ ይቀጥላል ወይንስ ወደ ሀዋሳ ያመራል የሚለው ቀጣይ ይጠበቃል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ