ሲዳማ ቡና ከ ሰበታ ከተማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

የዘጠነኛው ሳምንት መክፈቻ ጨዋታን አሰላለፍ የተመለከቱ መረጃዎችን እነሆ።

በሀዋሳ ከተማ ሽንፈት የገጠመው ሲዳማ ቡና የኋላ ክፍሉ ላይ  ባደረጋቸው ሁለት ቅያሪዎች ጉዳት የገጠመው የቀኝ መስመር ተከላካዩ ዮናታን ፍሰሀን በአማኑኤል እንዳለ እንዲሁም የመሀል ተከላካዩ ሰንደይ ሙቱኩን በጊት ጋትኮች በመተካት የዛሬውን ጨዋታ ይጀምራል።

አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ በባህር ዳሩ ጨዋታ በቀይ ካርድ የወጣባቸው የግራ መስመር ተከላካዩ ያሬድ ሀሰንን ቦታ በኃይለሚካኤል አደፍርስ ሲሸፍኑ ባደረጓቸው ሌሎች ለውጦች ምንተኖት አሎ ፣ አዲሱ ተስፋዬ እና ኢብራሂም ከድር በመሳይ ጳውሎስ ፣ አንተነህ ተስፋዬ እና ጉዳት በገጠመው ፉዓድ ፈረጃ ምትክ በአሰላለፉ ተካተዋል።

ሁለገቡ ኢብራሁም ከድር በዓመቱ የመጀመሪያ ጨዋታውን የሚጀምር ይሆናል።

ጨዋታውን ኢንተርናሽናል ዳኛ ኃይለየሱስ ባዘዘው በመሀል ካሳሀን ፍፁም እና እያሱ ካሳሁን በረዳት ዳኝነት ይመሩታል።

የቡድኖቹ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ሲዳማ ቡና

30 መሳይ አያኖ
3 አማኑኤል እንዳለ
2 ፈቱዲን ጀማል
24 ጊት ጋትኮች
12 ግሩም አሰፋ
16 ብርሀኑ አሻሞ
10 ዳዊት ተፈራ
29 ያስር ሙገርዋ
15 ተመስገን በጅሮንድ
9 ሀብታሙ ገዛኸኝ
27 ማማዱ ሲዲቤ

ሰበታ ከተማ

1 ምንተስኖት አሎ
5 ጌቱ ኃይለማርያም
4 አንተነህ ተስፋዬ
21 አዲሱ ተስፋዬ
23 ኃይለሚካኤል አደፍርስ
29 አብዱልባስጥ ከማል
6 ዳንኤል ኃይሉ
3 መስዑድ መሐመድ
9 ኢብራሂም ከድር
16 ፍፁም ገብረማርያም
7 ቡልቻ ሹራ


© ሶከር ኢትዮጵያ