ስምንተኛው ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ከቅዳሜ እስከ ሰኞ መደረጋቸው ይታወሳል። በነዚህ ጨዋታዎች ላይ ተመርኩዘን ያዘጋጀነውን ቁጥራዊ መረጃ እና ዕውነታ እነሆ!
– በዘህ ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች የተቆጠሩት ስምንት ጎሎች ብቻ ሲሆኑ የውድድር ዓመቱ እጅግ ዝቅተኛ የጎል መጠን ነው።
– ድሬዳዋ ከተማ በሦስት ጎሎች በርካታ ጎል ተጋጣሚው ላይ ያስቆጠረ ቡድን ሆኗል።
– ከስምንት ጎሎች መካከል የሙጂብ ቃሲም ብቻ በፍፁም ቅጣት ምት የተገኘ ሲሆን ሰባቱ በክፍት ጨዋታ ተቆጥረዋል።
– በዚህ ሳምንት የተቆጠሩት ሁሉም ጎሎት በሳጥን ውስጥ ተመተው የተቆጠሩ ናቸው።
– ስድስት ተጫዋቾች በዚህ ሳምንት የተቆጠሩ ጎሎች ባለቤት ናቸው። ፀጋዬ ብርሀኑ እና ሙኽዲነ ሙሳ ሁለት ጎል ሲያስቆጥሩ ሌሎች አራት ተጫዋቾች አንድ አንድ አስቆጥረዋል።
– አራት ተጫዋቾች ለጎል በማመቻቸት ተሳትፎ አድርገዋል። የድሬዳዋ ከተማው ጁኒያስ ናንጄቦ ሁለት በማመቻቸት ቀዳሚ ነው።
– ሙጂብ ቃሲም በዚህ ሳምንትም ጎል አስቆጥሮ ሰባተኛ ተከታታይ ጨዋታ ኳስን ከመረብ ሲያገናኝ አቡበከር ናስር አራተኛ ተከታታይ ጨዋታ አስቆጥሯል።
– በዚህ ሳምንት ሁለት የፍፁም ቅጣት ምቶች መክነዋል። ምንይሉ ወንድሙ እና ፍፁም ገብረማርያም ያመከኑት ተጫዋቾች ናቸው።
– የፋሲል ከነማው ግብ ጠባቂ ሚኬል ሳማኬ ያለፉት አራት ተከታታይ ጨዋታዎች ጎል ሳይቆጠርበት ወጥቷል።
የዲሲፕሊን ቁጥሮች
– በዚህ ሳምንት 25 የማስጠንቀቂያ ካርዶች ተመዘዋል።
– ዳንኤል ኃይሉ እና አስቻለው ታመነ በዚህ ሳምንት በቀይ ካርድ ከሜዳ የተወገዱ ተጫዋቾች ናቸው።
– ባህር ዳር ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያደረጉት ጨዋታ በ7 ቢጫ እና አንድ ቀይ ብዙ ካርድ የተመዘዘበት ጨዋታ ነው።
– ቅዱስ ጊዮርጊስ (3 ቢጫ እና 1 ቀይ) እንዲሁም ወላይታ ድቻ እና ባህር ዳር ከተማ (አራት ቢጫ) በርካታ ካርድ የተመለከቱ ቡድኖች ሆነዋል።
– እንድሪስ ሰዒድ፣ ሱራፌል ዳኛቸው እና ተስፋዬ አለባቸው የውድድር ዓመቱን አምስተኛ ቢጫ ካርድ በማየት ከፍተኛውን ቁጥር ይዘዋል። ቀጣይ ጨዋታም በቅጣት ምክንያት የሚያልፋቸው ይሆናል።
የሳምንቱ ስታቶች
(ቁጥሮቹ የተገኙት ከሱፐር ስፖርት ነው)
ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ
ከፍተኛ – ድሬዳዋ ከተማ – 9
ዝቅተኛ – ሀዲያ ቶሳዕና – 0
ጥፋቶች
ከፍተኛ – ፋሲል ከነማ – 27
ዝቅተኛ – ኢትዮጵያ ቡና – 12
ከጨዋታ ውጪ
ከፍተኛ – ፋሲል ከነማ – 7
ዝቅተኛ – ቡና እና ሆሳዕና – 0
የማዕዘን ምት
ከፍተኛ – ፋሲል ከነማ – 9
ዝቅተኛ – ወልቂጤ – 1
የኳስ ቁጥጥር ድርሻ
ከፍተኛ – ኢትዮጵያ ቡና – 65%
ዝቅተኛ – ወላይታ ድቻ – 35%
© ሶከር ኢትዮጵያ