በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዘጠነኛ ሳምንት የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ቡድኖቹ የሚጠቀሙበትን አሰላለፍ እና ሌሎች መረጃዎች እንዲህ አሰናድተናል።
ወላይታ ድቻ በቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 ከተሸነፈበት አሰላለፍ አሰልጣኝ ዘላለም ሺፈራው የሦስት ተጫዋቾችን ለውጥ ያረጉ ሲሆን በዚህም መልካሙ ቦጋለ፣ እንድሪስ ሰዒድ እና ቢኒያም ፍቅሬን አሳርፈው ፀጋዬ አበራ፣ ቸርነት ጉግሳ እና መሳይ ኒኮልን ወደ መጀመርያ አሰላለፍ አምጥተዋል። ከወጣት ቡድኑ ያደገው መሳይ በዓመቱ ለመጀመርያ ጊዜ ጨዋታ የሚጀምርም ይሆናል።
አሰልጣኝ ዘላለም ከጨዋታው በፊት በሰጡት አስተያየት ሥራቸውን በተረከቡ ማግስት በተከታታይ ጠንካራ ቡድኖችን መግጠማቸው ፈታኝ ቢሆንም የራሱ የሆነ በጎ ጎን እንዳለው ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ ቡና ባለፈው የጨዋታ ሳምንት ጅማ አባ ጅፋርን 3-1 ከረታው ስብስብ አሰልጣኝ ካሣዬ አራጌ ለዚህ ጨዋታ ምንም የተጫዋች ለውጥ ሳያደርጉ ቀርበዋል።
አሰልጣኝ ካሣዬ ከጨዋታው በፊት በሰጡት አስተያየት ክፍተት ቢኖርም ተጫዋቾቹ ሒደቱን አስጠብቀው እየሄዱበት ያለው መንገድን እንደ ጥንካሬ አንስተው በቀጣይ ቡድኑን እያሻሻሉ እንደሚጓዙ ተናግረዋል።
ጨዋታውን ዓለም አቀፍ ዳኛ ብሩክ የማነብርሀን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።
የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ ይህንን ይመስላል:-
ወላይታ ድቻ
99 መክብብ ደገፉ
9 ያሬድ ዳዊት
12 ደጉ ደበበ
26 አንተነህ ጉግሳ
16 አናጋው ባደግ
20 በረከት ወልዴ
6 ኤልያስ አህመድ
4 ፀጋዬ ብርሀኑ
22 ፀጋዬ አበራ
21 ቸርነት ጉግሳ
14 መሳይ ኒኮል
ኢትዮጵያ ቡና
1 ተክለማርያም ሻንቆ
18 ኃይሌ ገብረትንሳይ
4 ወንድሜነህ ደረጄ
2 አበበ ጥላሁን
11 አሥራት ቱንጆ
8 አማኑኤል ዮሐንስ
13 ዊልያም ሰለሞን
5 ታፈሰ ሰለሞን
10 አቡበከር ናስር
25 ሀብታሙ ታደሰ
17 አቤል ከበደ
© ሶከር ኢትዮጵያ