ከ20 ዓመት በታች የሊግ ውድድር የሚጀምርበት ተለዋጭ ቀን ታውቋል

በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የበላይነት የሚከወነው ከ20 ዓመት በታች የሊግ ውድድር የሚጀመርበት ቀን ተገልጿል።

ከ2008 ጀምሮ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የበላይነት መደረግ የጀመረውን ከ20 ዓመት በታች ውድድር ዓምና በኮቪድ-19 ምክንያት የመጀመሪያ ዙሩን ካጠናቀቀ በኋላ መቋረጡ ይታወሳል። ዘንድሮ የሚደረገው ውድድርንም ለመከወን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከጥቅምት 9 ጀምሮ ምዝገባ ሲያደርግ ቆይቷል። እስካሁን ባለው መረጃ መሠረትም 16 ክለቦች ውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ምዝገባ አከናውነዋል።

ቀደም ብሎ ጥር 18 ይጀምራል ተብሎ የነበረው ውድድሩ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ጥር 30 እንደተገፋ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘው መረጃ ያመላክታል። በ16 ክለቦች መካከል የሚደረገው ውድድርም በሁለት ምድብ ተከፍሎ አዳማ እና አሰላ ላይ እንደሚደረግ ተነግሯል።


© ሶከር ኢትዮጵያ