አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራውን በቅርቡ የቀጠረው ወላይታ ድቻ ለሁለተኛው ዙር ራሱን ለማጠናከር እንቅስቃሴ ጀምሯል።
እንደ አጀማመሩ ውጤቱ ሳያምርለት ቀርቶ እየተንገዳገደ በሚገኝበት ወቅት ከሳምንታት በፊት አሰልጣኝ ደሳለኝ ደቻሳን እና ምክትላቸውን በማሰናበት አዲስ አሰልጣኝ የሾመው ወላይታ ድቻ በአሰልጣኝ ዘላለም ሽረፈራው እየተመራ መሻሻል እያሳየ ይገኛል። ይህን ተከትሎ የአንደኛው ዙር ተጠናቆ የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት ቡድኑ አሉበት በተባሉ ክፍተቶች ላይ ተጨማሪ ተጫዋቾች ለማምጣት ከወዲሁ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ሰምተናል።
ይህን ጉዳይ ለማስፈፀም እና የሚያስፈልጉ ተጫዋቾችን ለማነጋገር አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው እና የክለቡ የቦርድ አባላት በዚህ ሰዓት አዲስ አበባ የሚገኙ ሲሆን በዋናነት ትኩረት ባደረጉባቸው ቦታዎች ላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ተጫዋቾችን ለማስፈረም እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ለማወቅ ችለናል። በቀጣይ በድርድር ላይ የሚገኘው የዝውውር ጉዳይ ሲጠናቀቅ ዝርዝር መረጃዎችን የምናደርሳችሁ ይሆናል።
© ሶከር ኢትዮጵያ