ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሲዳማ ቡና – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

04፡00 ሲል በሚጀምረው ጨዋታ ቡድኖቹ የጠቀሙትን አሰላለፍ እና አስተያየቶችን ልናደርሳችሁ ወደናል።

በትክክለኛው ሰዓት ላይ ትክክለኛዎቹን ክፍተቶች አግኝቶ በፍጥነት እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው የተናገሩት አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስ ከባህር ዳሩ ጨዋታ ሦስት ለውጦችን አድርገዋል። በለውጦቹ ቅጣት ላይ የሚገኘው አስቻለው ታመነ በደስታ ደሙ የተተካ ሲሆን ጋዲሳ መብራቴ እና ሮቢን ንግላንዴ ደግሞ በአቤል ያለው እና አዲስ ግደይ ተለውጠዋል።

ሲዳማ ቡናዎች ሰበታን ካሸነፉበት ጨዋታ ግሩም አሰፋን በሰንደይ ሙቱኩ እንዲሁም ዳዊት ተፈራን በዮሴፍ ዮሐንስ ለውጠው ለጨዋታው ቀርበዋል። አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ ቡድናቸው እየተሻሻለ ቢሆንም በተለይም በማጥቃቱ ረገድ የሚቆራረጡ ቅብብሎች እንዳሉ እና ለማስተካከል ጥረት እንዳደረጉ ተናግረዋል።

ግብ ጠባቂው መሳይ አያኖ በማሟሟቅ ላይ ሳለ ጉዳት የገጠመው በመሆኑ በፍቅሩ ወዴሳ ተተክቷል።
ጨዋታውን ኢንተርናሽናል አርቢትር ብሩክ የማነብርሀን በመሐል ዳኝነት ይመሩታል።

የቡድኖቹ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ቅዱስ ጊዮርጊስ

1 ለዓለም ብርሀኑ
14 ሄኖክ አዱኛ
3 አማኑኤል ተርፋ
24 ኤድዊን ፍሪምፖንግ
6 ደስታ ደሙ
26 ናትናኤል ዘለቀ
5 ሀይደር ሸረፋ
17 አዲስ ግደይ
10 አቤል ያለው
28 አማኑኤል ገብረሚካኤል
9 ጌታነህ ከበደ

ሲዳማ ቡና

30 መሳይ አያኖ
3 አማኑኤል እንዳለ
2 ፈቱዲን ጀማል
24 ጊት ጋትኮች
32 ሰንደይ ሙቱኩ
16 ብርሀኑ አሻሞ
6 ዮሴፍ ዮሐንስ
29 ያስር ሙገርዋ
15 ተመስገን በጅሮንድ
9 ሀብታሙ ገዛኸኝ
27 ማማዱ ሲዲቤ


© ሶከር ኢትዮጵያ