የሆሳዕና እና ሰበታ ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ የቡድኖቹ አሠልጣኞች አስተያየታቸውን ለሱፐር ስፖርት ሰጥተዋል።
አሸናፊ በቀለ – ሀዲያ ሆሳዕና
ስለ ጨዋታው…
በመጀመሪያው አጋማሽ ያሰብነውን ታክቲካል ዲስፕሊን መተግበር አልቻልንም። ይህንን ተከትሎም የጨዋታ መንገዳችንን መቀየር ነበረብን።
ስለ ፍፁም ቅጣት ምቱ…
ለአጋጣሚው ከእኔ የተሻለ ዳኞቹ ቅርብ ናቸው። ዳኛን መውቀስ ብዙም አይመቸኝም። ውሳኔው የዳኛው ነው።
ስለ ቡድኑ የጨዋታ መንገድ…
ዛሬ ስለ ጥንቃቄ አላሰብኩም። ለማጥቃት ነበር ወደ ሜዳ የገባነው። በጨዋታውም በሦስት አጥቂ ነበር የተጫወትነው። ያለንን ሃይል ተጠቅመን ነው የተጫወትነው።
አብርሃም መብራቱ – ሰበታ ከተማ
የጨዋታው መገባደጃ ላይ ስለተፈጠረው አጋጣሚ…
የፍፁም ቅጣት ምት ነው ብዬ ለመናገር በጣም እቸገራለሁ። ፍፁም ቅጣት ምቱንም በዳግም ምልከታ አይቼዋለው። የእውነት አምላክ አውጥቶናል። ግን ስለ ዳኝነቱ ብዙ ባልል ይሻለኛል።
ስለ ጨዋታው…
በመጀመሪያው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ አድርገናል። በሁለተኛው አጋማሽ ግን መሱድን የመሰሉ ፈጣሪ ተጫዋቾች ሲወጡብን የመሳሳቱ ሁኔታ ነበር። እንደታየውም የሜዳ ላይ መሪ አልነበረንም። ይህንን ተከትሎ ተጫዋቾቻችን አቻን ፍለጋ ትንሽ አፈግፍገው ነበር። ከዚህ የተነሳ በሁለተኛው አጋማሽ ትንሽ ጫና ነበረብን።
© ሶከር ኢትዮጵያ