ከደቂቃዎች በኃላ የሚጀምረው ጨዋታ አሰላለፍ እና ሌሎች ጉዳዮችን እነሆ።
ጨዋታው አሸናፊነትን ከማስቀጠል አንፃር ያለውን ፋይዳ አንስተው ቡድናቸው ያለበትን ደረጃ ከተጋጣሚያቸው አቅም አንፃር ገምተው እንደሚገቡ የገለፁት አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ኢትዮጵያ ቡናን ሲረቱ ከተጠቀሙበት አሰላለፍ አራት ለውጦች አድርገዋል። በዚህም መልካሙ ቦጋለ ፣ መሳይ አገኘው ፣ ነጋሽ ታደሰ እና ቢኒያም ፍቅሩ ጨዋታውን ሲጀምሩ ኤልያስ አህመድ ፣ ፀጋዬ አበራ ፣ ቸርነት ጉግሳ እና መሳይ ኒኮል አርፈዋል።
አሰልጣኝ የሱፍ ዓሊ በአንድ ሳምንት ዕረፍት ውስጥ በተቃራኒ ሜዳ ላይ የመገኘት ችግራቸውን ለመቅረፍ ሲሰሩ መሰንበታቸውን ተናግረዋል። ከመጨረሻው የቡና ጨዋታውም ሦስት ለውጦችን አድርገዋል። አሰልጣኙ ለወጣቱ ቤካም አብደላ የመጀመሪያ ጊዜ የመሰለፍ ዕድል ሲሰጡ ተመስገን ደረሰ እና ሀብታሙ ንጉሴም ወደ አሰላለፉ መጥተዋል። ከድር ኸይረዲን ፣ አብርሀም እና ሮባ ወርቁ ደግሞ የተተኩ ተጫዋቼች ናቸው።
ጨዋታውን ኢንተርናሽናል ዳኛ ኃይለየሱስ ባዘዘው በመሀል ዳኝነት ለመምራት ተመድበዋል።
ቡድኖቹ ይዘውት የሚገቡት የመጀመሪያ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል ;-
ጅማ አባ ጅፋር
1 ጄኮ ፔንዜ
2 ወንድምአገኝ ማርቆስ
16 መላኩ ወልዴ
14 ኤልያስ አታሮ
19 ተመስገን ደረሰ
21 ንጋቱ ገብረሥላሴ
20 ሀብታሙ ንጉሴ
8 ሱራፌል ዐወል
10 ሙሉቀን ታሪኩ
11 ቤካም አብደላ
17 ብዙዓየሁ እንዳሻው
ወላይታ ድቻ
99 መክብብ ደገፉ
9 ያሬድ ዳዊት
16 መልካሙ ቦጋለ
12 ደጉ ደበበ
26 አንተነህ ጉግሳ
16 አናጋው ባደግ
20 በረከት ወልዴ
4 ፀጋዬ ብርሀኑ
27መሳይ አገኘሁ
18 ነጋሽ ታደሰ
13 ቢኒያም ፍቅሩ
©ሶከር ኢትዮጵያ