ደደቢት ከ ድሬዳዋ ከተማ ፡ ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ደደቢት 2-0 ድሬዳዋ ከተማ
11’28’ ሽመክት ጉግሳ
– – – – – –
ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በደደቢት 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

90′ ተጨማሪ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

84′ ዳዊት ፍቃዱ ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

83′ የተጫዋች ቅያሪ – ደደቢት
ሁለቱንም ግቦች ያስቆጠረው ሽመክት ወጥቶ ኤፍሬም ጌታቸው ገብቷል፡፡

77′ ብርሃኑ የመታውን ቅጣት ምት ታሪክ ጌትነት በቀላሉ ይዞታል፡፡

76′ ታሪክ ጌትነት ከግብ ክልሉ ወጥቶ በሰራው ጥፋት ማስጠንቀቅያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

*ጨዋታው የተቀዛቀዘ እና የግብ ሙከራ የማይታይበት ሆኗል፡፡

60’የተጫዋች ቅያሪ – ድሬዳዋ ከተማ
በድሩ ኑርሁሴን ረመዳን ናስርን ቀይሮ ገብቷል፡፡

59′ የተጫዋች ቅያሪ – ደደቢት
ሄኖክ መኮንን ወጥቶ ያሬድ ብርሃኑ ገብቷል፡፡

52′ የተጫዋች ቅያሪ – ደደቢት
በጨዋታው ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው ያሬድ ዝናቡ ወጥቶ ሄኖክ ካሳሁን ገብቷል፡፡

የእረፍት ሰአት ቅያሪ – ድሬዳዋ ከተማ
ከድር አዩብ ወጥቶ ከሊፋ መሃመድ ገብቷል፡፡

ተጀመረ!!!
ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሯል፡፡
– – – – –

ተጠናቀቀ!!!
የመጀመርያው አጋማሽ በደደቢት 2-0 መሪነት ተጠናቀቀ፡፡

45+2′ ዳዊት ፍቃዱ የተከላካዮችን አለመናበብ ተጠቅሞ የሞከረውን ኳስ ሳምሶን እንደምንም አድኖታል፡፡

45′ ፍቃዱ ወርቁ ከማዕዘን ምት በግንባሩ የገጨው ኳስ በብርሃኑ ቦጋለ ተመልሶበታል፡፡

43′ የተጫዋች ለውጥ – ድሬዳዋ ከተማ
ፍቃዱ ወርቁ ፍሬው ብርሃንን ቀይሮ ገብቷል፡፡

41′ ሄኖክ አዱኛ በግምት ከ30 ሜትር የተገኘውን ቅጣት ምት በቀጥታ መትቶ በግቡ አናት ወጥቶበታል፡፡

39′ ፍቃዱ ታደሰ የመጀመርያውን የማስጠንቀቅያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

32′ ብርሃኑ ቦጋለ ከዳዊት የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

28′ ጎልልል!!!! ደደቢት
ሽመክት ጉግሳ በቀኝ መስመር በግምት ከ18 ሜትር የመታው ኳስ በግሩም ሁኔታ ከመረብ አርፏል፡፡

23′ ፍቃዱ ታደሰ ከአክሌስያ የተሻገረለትን ኳስ ሞክሮ ታሪክ ወደ ውጪ አውጥቶበታል፡፡ ከማዕዘን ምት የተሻማውን ኳስ ይሁን ሞክሮ የግቡን ቋሚ ታካ ለጥቂት ወጥታለች፡፡

11′ ጎልልል!!! ደደቢት
ሽመክት ጉግሳ ከቅጣት ምት የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ ደደቢትን ቀዳሚ አድርጓል፡፡

9′ አክሌስያ ግርማ ከዮናስ የተሻገረለትን ኳስ በፍጥነት አግኝቶ ቢሞክርም ታሪክ ጌትነት አድኖበታል፡፡

ተጀመረ
ጨዋታው በደደቢት ጀማሪነት ተጀምሯል፡፡

11:25 ሁለቱም ቡድኖች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡
– – – – –
የድሬዳዋ ከተማ አሰላለፍ
ሳምሶን አሰፋ
ሄኖክ አዱኛ – ሽመልስ አበበ – ብርሃኑ ሆራ – ፍሬው ብርሃን
ይሁን እንዳሻው – ከድር አዩብ – ዮናስ ገረመው
አክሌስያ ግርማ – ፍቃዱ ታደሰ – ረመዳን ከሪም

የደደቢት አሰላለፍ
ታሪክ ጌትነት
ስዩም ተስፋዬ – አይናለም ሃይለ – አክሊሉ አየነው – ተካልኝ ደጀኔ
ሽመክት ጉግሳ – ያሬድ ዝናቡ – ሳምሶን ጥላሁን – ብርሃኑ ቦጋለ
ዳዊት ፍቃዱ – ሄኖክ መኮንን
– – – – –

ያጋሩ