ቅዱስ ጊዮርጊስ ማስጠንቀቂያ እና የዲሲፕሊን ውሳኔ አሳለፈ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአጥቂው ሳላዲን ሰዒድ ላይ የዲሲፕሊን ውሳኔ ሲያስተላልፍ አሰልጣኙን ማስጠንቀቁን አስታውቋል።

ክለቡ በፌስቡክ ገፁ ይፋ ያደረገው መረጃ ይህን ይመስላል 👇

የቅዱስ ጊዮርስ ስፖርት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ በ2013 ዓ.ም የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለሚሳተፈው ቡድን ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ በተሟላ ሁኔታ ውጤታማ እንዲሆን በሁሉም መስኮች አስፈላጊውን ሁሉ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ ክለባችን ከተደረገለትና ከሚጠበቅበት ውጤታማነት አንጻር አርኪ የሚባል እንቅስቃሴዎችን እያደረገ አይደለም፡፡የስራ አመራር ቦርዱ በቅርቡ ባደረገው ስብሰባ በቡድኑ ውስጥ ያሉ ችግሮችን በተመለከተ ሰፊና ጥልቅ ውይይት አድርጎ፣ የተለያዩ የእርምት እርምጃዎች እንዲወሰዱ መመሪያዎችን ሰጥቷል፡፡

በቅርቡም የቡድኑ አልጣኝ ዳቪድስ ማሂር በቡድኑ ውስጥ ያሉ ችግሮችን በአፋጣኝ እንዲያስተካክሉ ከጅማ ወደ አዲስ አበባ በመጥራት በቦርዱ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ቦርዱ በተጨማሪም የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች የሆነው ሳላህዲን ሰኢድ በተደጋጋሚ ጊዜ የፈጸማቸውን የዲስፕሊን ግድፈቶች በአንክሮ በማየት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ አድርጓል፡፡

ሳላህዲንን ከዋናው ቡድን ጋር ለተጨማሪ ጊዜ አብሮ እንዲቆይ መፍቀድ በውድድሩ ላይ እየተፋለመ ለሚገኘው ቡድናችን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ስለሚያመዝን ከቡድን መሪው በሥነ ምግባር ዙሪያ በዝርዝር በሚቀርበው ሪፖርት ላይ በቦርዱ ውሳኔ እስከሚገኝ ድረስ ከተስፋ ቡድን ጋር ልምምዱን እያደረገ እንዲቆይ መመሪያ ተሰጥቷል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ