- በ 2011 የውድድር ዘመን ፕሪምየር ሊጉ በተገናኙባቸው ሁለት ጨዋታዎች በመጀመሪያው ዙር 1-1 በሆነ ውጤት ሲለያዩ በሁለተኛው ዙር ጅማ አባ ጅፋር ከሜዳው ውጪ 1-0 መርታት ችሎ ነበር።
ቅድመ ዳሳሳ | ባህር ዳር ከተማ ከ ጅማ አባ ጅፋር
የነገ ረፋዱን ጨዋታ የተመለከቱ ጉዳዮችን እንዲህ አንስተናል።
ባህር ዳር ከተማ ከመዲናዋ ክለቦች ጋር ባደረጋቸው ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ነጥብ ከተጋራ በኋላ የነገውን ጨዋታ ያደርጋል። ድል ከቀናውም አንድ ደረጃ የማሻሻል ዕድል ይኖረዋል።
ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች የተጋጣሚዎቹን አቀራረብ መሰረት ያደረገ የጨዋታ ዕቅድን ይዞ የገባው ባህር ዳር ከተማ ነገ ወደ ራሱ አጨዋወት ተመልሶ ከፍ ባለ ማጥቃት ወደ ሜዳ እንደሚገባ ይጠበቃል። ተጋጣሚው ካለበት ደካማ የመከላከል አደረጃጀት አንፃርም በቡድኑ የማጥቃት ሂደት ላይ ዋና ተዋናይ የሆኑ ተጨዋቾች ሊደምቁ የሚችሉበት ዕድል ይኖራል። ከሰሞኑ ተቀዛቅዞ የታየው የመስመር ተከላካዮቹ የማጥቃት ተሳትፎም ከፍ ማለቱ የሚቀር አይመስልም። ያም ቢሆን ከኋላ ሊፈጠሩ የሚችሉ ክፍተቶችን በአግባቡ ለመድፈን ጥንቃቄ ካላደረገ በሊጉ አንድ አንድ ጨዋታዎች ላይ እንደሚታየው በደካማው ተጋጣሚው አይቀጣም ማለት ከባድ ነው። ከዛ ውጪ ባህር ዳር በጨዋታዎች መካከል የሚታይበት መቀዛቀዝ እና ዕድሎችን የማባከን ችግር ካልታረመ ውጤቱ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድርበት ይችላል።
ጅማ አባ ጅፋር በከተማው ላይ ሲሰናበት ከከረመው ውድድር ውጤት የማግኘት የመጨረሻ ዕድሉን ይሞክራል። ቡድኑ አዲስ አበባ ላይ ከሀዋሳ እና ሰበታ ነጥብ ከተጋራ ወዲህ ተጨማሪ ነጥብ ለማግኘት አለመቻሉ ይታወቃል።
ከሜዳ ውጪ ያሉት ችግሮች ሰላባ የሆነው ጅማ አሁንም በሜዳ ላይ የተዳከመ እንቅስቃሴ በማሳየቱ ቀጥሏል። በቅድድሩ መሀከል ላይ ይታይበት የነበረው ጥብቅ መከላከል ላይ ያተኮረ አጨዋወት አንፃር ሰሞኑን በመጠኑ ለማጥቃትም ትኩረት የሰጠ አቀራረብ ይዞ ቢታይም ውጤት እንደራቀው ቆይታል። የቆሙ ኳሶችን የመከላከል አቅሙ እጅግ የወረደው ቡድኑ በመከላከል ሽግግር ወቅትም የተበታታነ አቃቋም ይታይበታል። እነዚህ ጉዳዮች ከነገ ተጋጣሚው አንፃር እጅግ አደጋ ላይ የሚጥሉ ሲሆን በማጥቃቱ በኩልም በግል ጥረት ከሚገኙት ግቦች ውጪ የቡድኑ የፊት መስመር እንቅስቃሴ መናበብ ርቆታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ጅማ እንደ አዳማ ድንገተኛ ልዩ ብቃት ይዞ አይመጣም ብሎ መደምደም ከባድ ነው።
በጨዋታው ባህር ዳር ከተማ ሳምሶን ጥላሀን እና አቤል ውዱ ከጉዳት ያልተመለሱለት ሲሆን በጅማ በኩል ያለውን የቡድን ዜና ግን ማግኘት አልቻልንም።
የእርስ በእርስ ግንኙነት