04፡00 ሲል በሚጀምረው ጨዋታ ዙሪያ የመጨረሻ መረጃዎችን ይዘንላችሁ ቀርበናል።
ድሬዳዋ ከተማን 3-1 መርታት የቻሉት አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው እያንዳንዱ ጨዋታ የራሱ ገፅታ እንዳለው ዛሬም ጠንካራ እና ተመልካቹ የሚዝናናበት ጨዋታ እንደሚሆን የጠቆሙ ሲሆን በዛሬው ጨዋታ ላይ ሦስት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም ከጉዳት የተመለሱት ተስፋዬ ነጋሽ እና ሀብታሙ ሸዋለም እንዲሁም ተቀይሮ ገብቶ ከፍ ያለ አስተዋፅዖ ያበረከተው አሜ መሀመድ ወደ ቀዳሚው አሰላለፍ መጥተዋል። ጉዳት የገጠማቸው አሳሪ አልመሀዲ እና ስዩም ተስፋዬ እንዲሁም ያሬድ ታደሰ ደግሞ ጨዋታውን አይጀምሩም።
በአዳማ ከተማ ያልተጠበቀ ሽንፈት ያስተናገዱት አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ለጨዋታው መዘጋጀታቸውን እና ከጉዳት የተመለሱ ተጫዋቾችን ማግኘታቸው እንደሚያግዛቸው የገለፁ ሲሆን ዛሬ አራት ተጫዋቾችን ለውጠው ቀርበዋል።
በዚህም ለውጥ ጉዳት ያስተናገደው ደስታ ዮሐንስ ፣ አዲስዓለም ተስፋዬ ፣ ጋብሪል አህመድ እና ሄኖክ ድልቢ ከአሰላለፍ ሲወጡ ከጉዳት የተመለሱት ዳንኤል ደርቤ ፣ ዳዊት ታደሰ ፣ ኤፍሬም ዘካርያስ እና ዘነበ ከድር ጨዋታውን ይጀምራሉ።
ፌደራል ዳኛ ተከተል ተሾመ ጨዋታውን በመኃል ዳኝነት የመምራት ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል
ሁለቱ ቡድኖች ወደ ሜዳ ይዘዉት የሚገቡት አሰላለፍ ይህንን ይመስላል
ወልቂጤ ከተማ
1 ጀማል ጣሰው
12 ተስፋዬ ነጋሽ
30 ቶማስ ስምረቱ
19 ዳግም ንጉሤ
3 ረመዳን የሱፍ
15 ተስፋዬ መላኩ
21 ሀብታሙ ሸዋለም
14 አብዱልከሪም ወርቁ
8 አቡበከር ሳኒ
7 አሜ መሀመድ
26 ሄኖክ አየለ
ሀዋሳ ከተማ
1 ሜንሳህ ሶሆሆ
7 ዳንኤል ደርቤ
4 ምኞት ደበበ
26 ላውረንስ ላርቴ
2 ዘነበ ከድር
18 ዳዊት ታደሰ
29 ወንድምአገኝ ኃይሉ
3 ኤፍሬም ዘካርያስ
21 ኤፍሬም አሻሞ
17 ብሩክ በየነ
10 መስፍን ታፈሰ
© ሶከር ኢትዮጵያ