የዕለቱን ቀዳሚ ጨዋታ የተመለከቱ የመጨረሻ መረጃዎችን እንድትካፈሉ ጋብዘናል።
በጉዳት እና በኮቪድ ሲቢያ ያጧቸውን ተጨዋቾች በቦታቸው የተተኩ ተጨዋቾች እንደሚሸፍኑ እና አሸንፈው ደረጃቸውን እንደሚያሻሽሉ እምነታቸው መሆኑን የገለፁት አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ከፋሲሉ ጨዋታ የአራት ተጨዋሾች ለውጥ አድርገዋል። በለውጦቹ ዳንኤል ደርቤ ፣ ዮሃንስ ሴጌቦ ፣ ኤፍሬም ዘካርያስ እና አለልኝ አዘነን በመተካት ፀጋአብ ዮሃንስ ፣ ደስታ ዮሃንስ ፣ ጋብርኤል አህመድ እና ወንድምአገኝ ኃይሉ ወደ መጀመሪያው አሰላለፍ መጥተዋል።
አዲሱን ኃላፊነታቸውን ዛሬ የሚጀምሩት አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ለጊዜው ቡድኑን በነበረበት የማስቀጠል እና ቀስ በቀስ ለውጦችን የማድረግ ሀሳብ እንዳላቸው ተናግረዋል። አሰልጣኙ ቡድኑ ጅማ ላይ ካከናወነው የመጨረሻ ጨዋታ ምንያምር ጴጥሮስን በያሬድ ዘውድነህ እንዲሁም አስጨናቂ ሉቃስን በእንዳለ ከበደ በመለወጥ ለመጀመር ወስነዋል።
ፌደራል ዳኛ ገመቹ ኢድኦ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት የሚመሩት አርቢትር ናቸው።
ቡድኖቹ ወደ ሜዳ ይዘውት የሚገቡት የመጀመሪያ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል።
ድሬዳዋ ከተማ
30 ፍሬው ጌታሁን
2 ዘነበ ከበደ
14 ያሬድ ዘውድነህ
21 ፍሬዘር ካሣ
4 ሄኖክ ኢሳይያስ
5 ዳንኤል ደምሴ
8 ሱራፌል ጌታቸው
11 እንዳለ ከበደ
17 አስቻለው ግርማ
99 ሙኅዲን ሙሳ
20 ጁንያስ ናንጄቦ
ሀዋሳ ከተማ
1 ሜንሳህ ሶሆሆ
44 ፀጋአብ ዮሃንስ
4 ምኞት ደበበ
26 ላውረንስ ላርቴ
12 ደስታ ዮሃንስ
18 ዳዊት ታደሰ
5 ጋብርኤል አህመድ
29 ወንድምአገኝ ኃይሉ
21 ኤፍሬም አሻሞ
17 ብሩክ በየነ
10 መስፍን ታፈሰ
© ሶከር ኢትዮጵያ