የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ተስፋሁን ጋዲሳ (ኮል) ከዓመታት አስቸጋሪ ህይወት በኃላ ለሀገሩ በቅቷል።
ባለክህሎቱ ተስፋሁን ጋዲሳ በኢትዮጵያ ቡና፣ አየር መንገድ፣ መከላከያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከተጫወተ በኋላ ወደ የመን ክለብ ቢያቀናም እጅግ ያልጠበቀው ሁኔታ ተፈጥሮ ከባለቤቱ እና ከሁለት ልጆቹ ጋር በርዕስ በዕርስ ጦርነት በምትታመሰው የመን ለዓመታት አስቸጋሪ ህይወት ሲገፋ መቆየቱ ይታወቃል። ወደ ትውልድ ሀገሩ ለመመለስ መቸገሩን ተከትሎም የተለያዩ ርብርቦሽ ሲደረግ ቆይቶ ትናንት ማምሻውን ወደ ሚናፍቃት ሀገሩ በሰላም ተመልሷል።
ሶከር ኢትዮጵያ በቀጣይ ቀናት ተጫዋቹን አግኝታ ስለነበረበት ሁኔታ ለማናገር ጥረት እንደምታደርግ ከወዲሁ እንገልፃለን።
© ሶከር ኢትዮጵያ