ወልቂጤ ከተማ በዘንድሮ የውድድር ዓመት ወደ ቡድኑ ከቀላቀላቸው ሦስት ተጫዋቾች ጋር በስምምነት ለመለያየት ተቃርቧል።
ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ጥሩ የውድድር ጅማሮ እያደረገ የሚገኘው ወልቂጤ ከተማ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ሥዩም ተስፋዬ፣ አሚኑ ነስሩ እና አብዱራህማን ሙባረክን ማስፈረሙ ይታወቃል። ሆኖም ከተጫዋቾቹ ጋር ለጊዜው ባልተገለፀ ጉዳይ ከክለቡ ጋር በስምምነት ሊለያዩ እንደሆነ የታወቀ ሲሆን ወደ ባህር ዳር ካቀናው የቡድኑ ስብስብ ውጭ በመሆን አለመጓዛቸውን አረጋግጠናል።
በአሁኑ ወቅት ከቡድኑ አመራሮች ጋር እየተደራደሩ ሲሆን በቅርብ ቀናትም በስምምነት የመለያየታቸው ነገር የሚጠበቅ ይሆናል።
© ሶከር ኢትዮጵያ