ካለበት የውጤት ቀውስ ራሱን ለማውጣት በሁለተኛው ዙር ወደ ዝውውሩ እንደሚገባ የሚጠበቀው አዳማ ከኢትዮጵያ ቡና አንድ ተጫዋች አስፈርሟል።
በርከት ያሉ ተጫዋቾችን አሰናብቶ የዛኑ ያህል ብዛት ያላቸው ተጫዋቾች እንደሚያስፈርም እየተነገረ የሚገኘው አዳማ ከተማ በኢትዮጵያ ቡና ብዙም የመሰለፍ ዕድል ያላገኘው አጥቂ ሰይፈ ዛኪርን አስፈርሟል። በ2012 መጀመርያ ከፌዴራል ፖሊስ ኢትዮጵያ ቡናን ከተቀላቀለ በኃላ እምብዛም መጫወት ያልቻለው ሰይፈ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በቅርቡ በስምምነት ከተለያየ በኃላ ማረፊያውን አዳማ ከተማ አድርጓል።
አዳማ ከተማ በቀጣዮቹ ቀናት ራሱን ለማጠናከር ብዛት ካላቸው ተጫዋቾች ጋር እየተደራደር መሆኑን ሰምተናል።
© ሶከር ኢትዮጵያ