አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ረዳታቸውን አሳወቁ
የወላይታ ድቻ አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ረዳት አሰልጣኛቸውን መርጠዋል።
ዋናውና ምክትል አሰልጣኙን ያሰናበተው ወላይታ ድቻ አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራውን ከቀጠረ አንድ ወር ማስቆጠሩ ይታወቃል። ቡድኑን ከተረከቡበት ጊዜ አንስቶ በማጠናከር የተጠመዱት አሰልጣኙ ዛሬ አሰልጣኝ ዳዊት ሀብታሙን ረዳታቸው አድርገው መምረጣቸው ታውቋል።
ወጣቱ አሰልጣኝ ዳዊት ሀብታሙ በአዳማ ተስፋ ቡድን በጀመረው የአሰልጣኝነት ህይወቱ በርካታ ወጣቶችን በማፍራት የሚታወቅ ሲሆን በመቀጠል በለገጣፎ ለገዳዲ ከረዳት አሰልጣኝነት እስከ ዋና አሰልጣኝነት ያለፉትን አምስት ዓመታት አገልግሏል። ከ2011 ጀምሮ በዋና አሰልጣኝነት ቡድኑን ሲመራ የቆየው ዳዊት በዛው ዓመት ቡድኑን ለፕሪምየር ሊግ ለማብቃት እስከመጨረሻው ጨዋታ ሲፎካከር የነበረ ሲሆን ዓምናም ሊጉ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ ምድቡን ሲመራ ቆይቷል።
በቅርቡ ከለገጣፎ ጋር የተለያየው አሰልጣኙ ነገ ወደ ባህር ዳር በማቅናት ከቡድኑ ጋር በመቀላቀል የአሰልጣኝ ዘላለም ረዳትነት ሥራን እንደሚጀምር ይጠበቃል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
ተዛማጅ ፅሁፎች
የአሰልጣኞች አስተያየት | ሀዲያ ሆሳዕና 2-2 ወላይታ ድቻ
ከጥሩ የሜዳ ላይ ፉክክር በኋላ ሁለት አቻ ከተጠናቀቀው ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል። አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት...
ሪፖርት | ወላይታ ድቻ እና ሀዲያ ሆሳዕና ነጥብ ተጋርተዋል
ጥሩ ፉክክር ያስተናገደው የምሳ ሰዓቱ የወላይታ ድቻ እና ሀዲያ ሆሳዕና ጨዋታ 2-2 በሆነ ውጤት ተጠናቋል። ሀዲያ ሆሳዕና ከቅዱስ ጊዮርጊሱ ጨዋታ...
የሴቶች ፕሪምየር ሊግ | የሊጉ መሪ ንግድ ባንክ እና ተከታዩ ኤሌክትሪክ ሲያሸንፉ ሀዋሳ እና መከላከያ ነጥብ ተጋርተዋል
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በአዳማ ሲከወኑ ሊጉን እየመራ የሚገኘው ንግድ ባንክ በግብ ሲንበሸበሽ ተከታዩ ኢትዮ ኤሌክትሪክ...
ቅድመ ዳሰሳ | የ29ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ሦስት ጨዋታዎች ቅድመ ምልከታ
የ29ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ሦስት ጨዋታዎችን እንደሚከተለው ቃኝተናቸዋል። በዘንድሮ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የዋንጫ ፉክክሩ እና ላለመውረድ ትንቅንቁ ቀጠሎ እስካለንበህ የ29ኛ...
አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ቅጣት ተላለፈባቸው
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንትን ተከትሎ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተወስነዋል። ሊጠናቀቅ የሁለት ሳምንት ዕድሜ የቀረው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...
አዳማ ከተማ ሁለት ተጫዋቾቹን ሸኝቷል
ከወረጅ ቀጠናው ለመውጣት እየጣረ የሚገኘው አዳማ ከተማ ሁለት ተጫዋቾቹን በዲሲፕሊን ምክንያት ከስብስቡ መቀነሱ ታውቋል። በ28ኛ ሳምንት ከመከላከያ ጋር ያለ ጎል...