ድሬዳዋ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ሾመ
ከአሰልጣኝ ፍስሀ ጥዑመልሳን ጋር የተለያየው ድሬዳዋ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ቀጥሯል።
የድሬዳዋ ከተማ ሴቶች ቡድን እና የወንዶች ቡድኑን በምክትል አሰልጣኝነት በማገልገል ካለፈው ዓመት አጋማሽ ጀምሮ ወደ ዋና አሰልጣኝነት ከፍ ያሉት አሰልጠኝ ፍስሐ ከቡድኑ ጋር ከተለያዩ በኋላ በዛሬው ዕለት በፌዴሬሽን በመገኘት አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስን መቅጠሩን አረጋግጧል።
አሰልጣኝ ዘማርያም ከዚህ ቀደም በአዳማ ከተማ፣ ፋሲል ከነማ፣ ወልድያ እና ጅማ አባ ጅፋር ማሰልናቸው የሚታወቅ ሲሆን በተሰረዘክ የውድድር ዓመት ወልዋሎን ተረክበው እንደነበር ይታወሳል።
አሰልጣኝ ዘማርያም የወጥነት ችግር የሚስተዋልበት እና በአሁኑ ወቅት በወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ ውጤትን የማሻሻል ፈተናቸውን በ13ኛ ሳምንት ሀዋሳ ከተማን በመግጠም የሚጀምሩ ይሆናል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
ተዛማጅ ፅሁፎች
የሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ተጠባቂው ጨዋታ ነጥብ በመጋራት ተጠናቋል
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ15ኛ ሳምንት ስድስት ጨዋታዎች ዛሬ በሁለት ስታዲየሞች ሲደረጉ ተጠባቂው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታ...
ድሬዳዋ ከተማ የዛሬውን ጨዋታ መነሻ በማድረግ ቅሬታውን አቅርቧል
በ28ኛው ሳምንት ከባህር ዳር ከተማ ጋር ቀትር ላይ የተጫወተው ድሬዳዋ ከተማ ለሊጉ የበላይ አካል የቅሬታ ደብዳቤ አስገብቷል። በባህር ዳር ስታዲየም...
ሪፖርት | ወልቂጤ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ነጥብ ተጋርተዋል
በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ እና ሲዳማ ቡና አንድ አቻ ተለያይተዋል። ባሳለፍነው ሳምንት በሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት ለምንም የተረቱት...
የአሠልጣኞች አስተያየት | ባህር ዳር ከተማ 1-0 ድሬዳዋ ከተማ
በወራጅ ቀጠናው ትልቅ ትርጉም ያለው ፍልሚያ በጣናው ሞገዶቹ አሸናፊነት ከተጠናቀቀ በኋላ የአሸናፊ ቡድን አሠልጣኝ አስተያየት ሲሰጡ የተሸናፊው ግን ፍቃደኛ ሳይሆኑ...
ቅድመ ዳሰሳ | የ28ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ፍልሚያዎች
የሳምንቱን ፍልሚያዎች የሚያስጀምሩት የነገ ሁለት መርሐ-ግብሮች እንደሚከተለው ዳሰናል። ባህር ዳር ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ በ26ኛ ሳምንት በሀዋሳ ከተማ እና አርባምንጭ...
ፌዴሬሽኑ የሻረውን ኃላፊነት ለሊግ ካምፓኒው መልሶ ሰጥቷል
ከሰሞኑ ውዝግብ ውስጥ ገብተው የነበሩት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና የፕሪምየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር ወደ ስምምነት መጥተዋል። የወልቂጤ ከተማው አምበል ጌታነህ...