ጅማ አባ ጅፋር የዕግድ ውሳኔ ተላለፈበት
አስቀድሞ የተስማሙበትን ስምምነት ተግባራዊ አላደረገም በሚል ፌዴሬሽኑ ጅማ አባ ጅፋር ላይ የዕግድ ውሳኔ አስተላለፈ።
ባሳለፍነው ዓመት ቡድኑን እያገለገሉ የነበሩ በርከት ያሉ ተጫዋቾች የሙሉ ክፍያ እና የወራት ክፍያ አልተፈፀመልንም በማለት ክስ መመስረታቸው ይታወቃል። በዚህም መሠረት ጅማ አባ ጅፋር ለተጫዋቾቹ ክፍያውን እስኪፈፅም ድረስ ፌዴሬሽኑ ማንኛውም አገልግሎት እንዳያገኝ ዓምና ዕግድ ማስተላለፉ ይታወቃል።
ሆኖም ክለቡ በተለያየ ጊዜ ደሞዛቸውን ለመክፈል ማሰቡን ባሸማጋዮች በኩል የመፍትሔ ሀሳብ በማቅረቡ ተጫዋቾቹ ይህን ሀሳብ ተቀብለው ቢስማሙም በተቀመጠው ቅድመ ስምምነት መሠረት እስካሁን ዕለት ደሞዛችን ሊከፈለን አልቻለም በማለት ለፌዴሬሽኑ ባቀረቡት አቤቱታ መሠረት ፌዴሬሽኑ ጅማ አባ ጅፋር ውሳኔውን ተግባራዊ እስኪያደርግ ከማንኛውም አገልግሎቶች ያገደ መሆኑን በደብዳቤ አሳውቋል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
ተዛማጅ ፅሁፎች
የሴቶች ፕሪምየር ሊግ | መከላከያ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዋሳ ወሳኝ ድል አሳክተዋል
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በተደረጉ አራት መርሐግብሮች ጅምሩን ሲያደርግ መከላከያ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዋሳ ተጋጣሚዎቻቸውን...
የአሰልጣኞች አስተያየት | አዳማ ከተማ 1-1 ድሬዳዋ ከተማ
በሊጉ ለመቆየት ብርቱ ትግል ተደርጎበት ነጥብ በመጋራት ከተጠናቀቀው ጨዋታ ፍፃሜ በኋላ አሰልጣኞች የድህረ-ጨዋታ አስተያየት ሰንዝረዋል፡፡ አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ - አዳማ...
ከ17 እና ከ15 ዓመት በታች ውድድሮች የሚደረጉበት ቦታ እና ቀን ይፋ ሆኗል
የ2014 ከ17 ዓመት በታች እና ከ15 ዓመት በታች የፓይለት ፕሮጀክት ውድድሮች የሚደረጉበት ከተማ እና ቀን ታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን...
የአዲስ አበባ ከተማ የቡድን አባላት ዝርፊያ ተፈፀመባቸው
በሲዳማ ቡና ሽንፈት ያስተናገድው የአዲስ አበባ ከተማ የቡድን አባላት ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ዝርፊያ እንደተፈፀመባቸው ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች። ረፋድ ላይ በ29ኛ...
የሴቶች ፕሪምየር ሊግ | የሊጉ መሪ ንግድ ባንክ እና ተከታዩ ኤሌክትሪክ ሲያሸንፉ ሀዋሳ እና መከላከያ ነጥብ ተጋርተዋል
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በአዳማ ሲከወኑ ሊጉን እየመራ የሚገኘው ንግድ ባንክ በግብ ሲንበሸበሽ ተከታዩ ኢትዮ ኤሌክትሪክ...
አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ቅጣት ተላለፈባቸው
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንትን ተከትሎ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተወስነዋል። ሊጠናቀቅ የሁለት ሳምንት ዕድሜ የቀረው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...