ሰበታ ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

ከከሰዓቱ ጨዋታ አስቀድሞ ተከታዮቹን መረጃዎች እንድታነቡ እንጋብዛለን።

አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ አዳማን በረታው ስብስባቸው ላይ አራት ለውጦች አድርገዋል። በዚህም ጌቱ ኃይለማርያም ፣ ዳዊት እስጢፋኖስ ፣ ቃልኪዳን ዘላለም እና ዱሬሳ ሹቢሳ አርፈው አለምአየሁ ሙለታ ፣ መስዑድ መሀመድ ፣ ኢብራሂም ከድር እና ፍዐድ ፈረጃ ወደ አሰላለፍ መጥተዋል። አሰልጣኙ በብሔራዊ ቡድን ኃላፊነታቸው ወቅት የባህር ዳር ሜዳ ላይ የነበራቸው መልካም ትዝታ እንደተቀሰቀሰባቸው ገልፀው ቡድናቸው በአካል ብቃት ለመጠንከር እና የጨዋታ ሀሳቡን ይዞ ለመቆየት የሚረዳ ዝግጅት ሲያደርግ እንዳሰነበተ ተናግረዋል።

ቡድናቸው ከጨዋታ ጨዋታ እየተሻሻለ እንደመጣ እና የተጨዋቾቹ መነሳሳት እንዲሁም የቡድን መንፈሱ ከፍ ያለ መሆኑን የገለፁት አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ከሀዋሳ ጋር ነጥብ ከተጋሩበት ጨዋታ ባደረጓቸው ሁለት ለውጦች ጉዳት የገጠማቸው ዳግም ንጉሴ እና ተስፋዬ ነጋሽን በይበልጣል ሽባባው እና ከጉዳት በተመለሰው ፍሬው ሰለሞን ቀይረዋል። በዚህም ይበልጣል ሽባባው የዓመቱን የመጀመሪያ ጨዋታውን ይጀምራል።

ጨዋታው በፌደራል ዳኛ ቢኒያም ወርቅአገኘሁ የመሀል ዳኝነት ይከናወናል።

የቡድኖቹ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ሰበታ ከተማ

1 ምንተስኖት አሎ
14 አለማየሁ ሙለታ
4 አንተነህ ተስፋዬ
13 መሳይ ጳውሎስ
23 ኃይለሚካኤል አደፍርስ
3 መስዑድ መሀመድ
15 አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ
17 ታደለ መንገሻ
8 ፍዐድ ፈረጃ
9 ኢብራሂም ከድር
16 ፍፁም ገብረማርያም

ወልቂጤ ከተማ

1 ጀማል ጣሰው
16 ይበልጣል ሽባባው
30 ቶማስ ስምረቱ
15 ተስፋዬ መላኩ
3 ረመዳን የሱፍ
21 ሀብታሙ ሸዋለም
14 አብዱልከሪም ወርቁ
13 ፍሬው ሰለሞን
8 አቡበከር ሳኒ
7 አሜ መሀመድ
26 ሄኖክ አየለ


© ሶከር ኢትዮጵያ