ፕሪሚየር ሊግ ፡ ደደቢት ወደ አሸናፊነት ሲመለስ አርባምንጭ ከፍተኛ ደረጃ ያሻሻለበትን ድል አስመዝግቧል

 

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት ሶስት ጨዋታዎች ዛሬ ተካሂደው አርባምንጭ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ድል ቀንቷቸዋል፡፡ ዳሽን አቻ ተለያይቶ ወራጅ ቀጠናውን ተቀላቅሏል፡፡

09፡00 ላይ ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ 3-1 አሸንፎ ከወራጅ ቀጠናው መውጣት ችሏል፡፡ ሲዳማ ቡና ጨዋታው በተጀመረ በ7ኛው ደቂቃ በኤሪክ ሙራንዳ አማካኝነት ቀዳሚ መሆን ቢችልም ተሾመ ታደሰ በ31ኛው ደቂቃ አዞዎቹን አቻ አድርጓል፡፡ ከእረፍት መልስ ተቀይሮ የገባው በረከት ወልደጻዲቅ ሁለተኛውን ሲያስቆጥር በጨዋታው መጠናቀቅያ ደቂቃዎች በሲዳማ ቡና የግብ ክልል የተሰራውን ጥፋት ተከትሎ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት ታደለ መንገሻ ወደ ግብነት ቀይሮ ጨዋታው በአርባምንጭ 3-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ባህርዳር ኢንተርናሽናል ስታድየም ላይ ሀዋሳ ከተማን ያስተናገደው ዳሽን ቢራ ካለግብ አቻ ተለያቷል፡፡ ይህ ውጤት በተከታታይ ጨዋታዎች ከድል የራቀው ዳሽን ቢራን ወደ ወራጅ ቀጠናው አስገብቶታል፡፡

11፡30 ላይ ድሬዳዋ ከተማን ያስተናገደው ደደቢት 2-0 አሸንፏል፡፡ የደደቢት የድል ግቦችን ከመረብ ያሳረፈው ፈጣኑ የመስመር አማካይ ሽመክት ጉግሳ ነው፡፡ ሽመክት ቀዳሚውን ግብ ከቅጣት ምት የተሸማውን ኳስ በግንባሩ በመግጨት ሲያስቆጥር ሁለተኛውን ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውጪ በመምታት በግሩም ሁኔታ አስቆጥሯል፡፡

የ12ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገ ፣ ሀሙስ እና አርብ ቀጥለው ይውላሉ፡፡

አአ ፡ ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዲያ ሆሳዕና (ሰኞ 11፡30)

አዳማ ፡ አዳማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (ሀሙስ 09፡00)

አአ ፡ ኤሌክትሪክ ከ ወላይታ ድቻ (ሀሙስ 11፡30)

(ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መከላከያ የሚያደርጉት ጨዋታ ሚያዝያ 3 ይደረጋል)

የደረጃ ሰንጠረዥ

PL

የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ደረጃ

Untitled

ያጋሩ