ጅማ አባ ጅፋር ከ ሲዳማ ቡና – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

ከደቂቃዎች በኋላ በሚጀምረው ጨዋታ የመጨረሻ መረጃዎችን እንድትካፈሉ ጋብዘናል።

በአሰልጣኝነት ሁል ጊዜ የተመቻቸ ሁኔታን ብቻ እንደማይጠብቁ የገለፁት አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነምህረት በዋናነት የቡድኑን ደካማ ጎኖች በሁለተኛው ዙር ለማጠናከር እንደሚጥሩ ገልፀዋል። ቡድናቸው ከባህር ዳር ከተማ ጋር ነጥብ ከተጋራበት ጨዋታ ባደረጓቸው ሁለት ለውጦችም ጉዳት የገጠመው ሀብታሙ ንጉሴን በሙሉቀን ታሪኩ፣ ሮባ ወርቁን በአብርሀም ታምራት በመተካት ጨዋታውን መጀመር መርጠዋል።

ወደ ሥራ ስለመመለስ እና በቡድኑ ውስጥ መሻሻል የሚችሉ ነገሮች በመመልከት ሲዳማን እንደተቀላቀሉ የገለፁት አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በኢትዮጵያ በና 5-0 ከተሸነፈው ቡድን ውስጥ ሁለት ለውጦች አርገው ቀርበዋል። በለውጦቹም ግርማ በቀለ እና አዲሱ አቱላ ከቅጣት በተመለሰው ፈቱዲን ጀማል እና ተመስገን በጅሮንድ ተቀይረዋል።

ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ይሚመሩት አርቢትር ቴዎድሮስ ምትኩ መሆናቸው ታውቋል።

ሁለቱ ቡድኖች ለዛሬው ጨዋታ ተከታዮቹን ተጫዋቾች በመጠቀም ወደ ሜዳ ይገባሉ።

ጅማ አባ ጅፋር

99 አቡበከር ኑሪ
2 ወንድምአገኝ ማርቆስ
16 መላኩ ወልዴ
23 ውብሸት ዓለማየሁ
14 ኤልያስ አታሮ
21 ንጋቱ ገብረሥላሴ
10 ሙሉቀን ታሪኩ
18 አብርሀም ታምራት
8 ሱራፌል ዐወል
7 ሳዲቅ ሴቾ
19 ተመስገን ደረሰ

ሲዳማ ቡና

1 ፍቅሩ ወዴሳ
3 አማኑኤል እንዳለ
2 ፈቱዲን ጀማል
24 ጊት ጋትኮች
12 ግሩም አሰፋ
16 ብርሀኑ አሻሞ
6 ዮሴፍ ዮሐንስ
10 ዳዊት ተፈራ
15 ተመስገን በጅሮንድ
9 ሀብታሙ ገዛኸኝ
27 ማማዱ ሲዲቤ


© ሶከር ኢትዮጵያ